Translation is not possible.

     ሌሊት ላይ ሰራዊቶች የሚያርፉባቸው ድንኳኖች ዙሪያ እየተዟዟረ ይቃኛቸዋል።

   በአንድ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ ለይል እየሰገዱ፣ ቁርኣን እየቀሩ ሲያያቸው;

   "በዚህ ነው ነስር የሚመጣው" ይላል።

  ወደ ሌላ ድንኳን ሲያቀና ውስጡ ያሉ ሰራዊቶች ተኝተው ፀጥጥጥ ያለ ከሆነ;

   "ከዚህ ነው ሽንፈት የሚመጣው" ይላል።

         🗡ሰላሑዲን አዩቢ

   እይልኝ ወዳጄ

  ሌሊት ላይ ለይል ሳይሰግድ እና ቁርኣን ሳይቀራ ተኝቶ ማደር የሽንፈት መንስኤ አድርገው ይቆጥሩት ነበር። እንደዚህ የነበሩት ናቸው ቁድስን ነፃ ያወጡት።

  ታድያ ሌሊቱ እየቃመ፣ እየዘፈነ፣ አርሴ ማንቼ እያለ፣ ቲክቶክ እና ዩትዩብ ላይ እየተጃጃለ የሚያነጋው ምን ሊባል ነው!?

አዎን!!

   ያለነው ጥፋት ላይ ነው። ሆኖም; የተመላሽ መመለስ የሚቀበል ጌታ ነውና ያለን ወደ አላህ እ ን መ ለ ስ !!

     

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group