1 year Translate
Translation is not possible.

በጣም የማረከኝ ክስተት!!

✍ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ። አብረው ጉዞ ወጡና አንድ ሆቴል ክላስ ይዘው አደሩ። በነጋታው ጠዋት ተነስተው ወደ ጉዳያቸው ሊወጡ ሲሉ አንደኛው ከያዘው ገንዘብ 100 ዲናር ያህል ይጠፋበታል።

ለጓደኛው

"ከኪሴ መቶ ዲናር ጠፍቶብኛል አይተህ ነበር እንዴ?" አለው።

ጓደኛው

"አዎን ለሊት ተነስቼ ነበር የሆነ ዕቃ መግዛት ፈለኩኝና ወስጄብሃለው።" አለው።

"ነው እንዴ? አብሽር" አለውና ወደ ጉዳያቸው አቀኑ።

ጉዳያቸውን ጨራርሰው ወደ ክላሳቸው ሲመለሱ የሆቴሉ የፅዳት ሰራተኛ ያገኛቸውና

"ክላሳችሁ ላፀዳ ስገባ 100 ዲናር ወድቆ አግኝቻለሁ" ብሎ ይሰጣቸዋል።

በዚህ ጊዜ ገንዘብ ጠፍቶት የነበረው በአግራሞት ወደ ጓደኛው ይዞርና "እኔ ወስጃለሁ ብለኸኝ አልነበር እንዴ?" አለው።

ጓደኛውም ሲመልስ:-

"እንደ ምታየው ከእኔና ከአንተ ውጪ ሌላ ሰው አልነበረም። አላየሁም ብልህ ኖሮ ሸይጣን በመሃላችን ገብቶ ስራውን ሊሰራ ይችላል። ያ እንዳይሆን 100 ዲናሩ በራሴ ላይ እዳ አድርጌው ጓደኝነታችን ለገንዘብ ሲባል እንዳይቋረጥ ልጠብቀው ብዬ ነው ወስጃለሁኝ ያልኩህ።" አለው።

ሷሊህ ታማኝ ጓደኛ ካለህ ትልቅ ፀጋ ነውና አደራህ ተንከባከበው‼️

https://ummalife.com/umma1698228713

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group