Translation is not possible.

ኢየሩሳሌም ዳግም በሙስሊሞች እጅ መልሳ የማትገባ ይመስላችሗል ??? አል አቅሷ መልሶ ነፃ የማይወጣ ይመስላችሗል ??!! አትጠራጠሩ !!!!

         👉 t.me/Seidsocial

የቅርቡን የዚህችን እጅግ ጥንታዊት ከተማ ታሪክ እናንሳ እንኳ ቢባል

፨ ለ በርካታ መቶ አመታት በባይዛንታይን ሮሞች አረመኔያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የቆየችው ቁድስ በነ ኻሊድ ኢብን ወሊድ እና አቡኡበይዳ ኢብን አልጀራህ የሚመራው ጦር ባይዛንታይኖችን አንበርክኮ ቁድስ ዳግም በሙስሊሞች እጅ ለመግባት ችላ ነበር ። የቁድስን ቁልፍ ቦታው ድረስ ሂደው የተቀበሉት ኡመር ኢብኑል ኸጧብ የቁድስን ነዋሪዎች ነፃነት አውጀው ነበር የተመለሱት ። ቁድስ ከዚያ በሗላ አበበች አሸበረቀች በፍትህና በኢስላማዊው ስልጣን ተንቆጠቆጠች ።

፨ በኡመር ጊዜ ሙስሊሞች ከተቆጣጠሯት በሗላ ቁድስ እስከ መጨረሻው በሙስሊሞች እጅ አልቆየችም ። የሙስሊሞችን መከፋፈልና እርስበርስ መባላት ተጠቅመው ባይዛንታይኖች ዳግም ቁድስን ተቆጣጠሩ ። ቁድስ ( ኢየሩሳሌም ) ዳግም የጨለማ ዘመን ውስጥ ገባች ። ከተማዋን በደል ግፍና ጭካኔ ሞላት !! በከተማዋ የሚስኪኖች ዋይታና የገዥዎች ከልክ ያለፈ አረመኔነት እንጅ አይሰማም አይታይም ነበር ! ቁድስ በባይዛንታይኖች እንደዚህ በበደል ተውጣ ቆዝማ አዝና ብዙ አመታትን አሳለፈች !!

፨ አሏህ #ሰልጁቅ የተሰኙ ቱርኮችን ከወደ ምስራቅ ኤዥያ አስነሳ ። የሰልጁቅ የልጅ ልጅ የሆኑት እነ ቱግሪል ፣ ቻግሪ ፣ አልፕ አርስላን ፣ መሊክ ሻህ የመሳሰሉ ተወዳዳሪ አልባ ጀግና የጦር መሪዎች የአለም ልእለሀያል የነበረውን የባይዛንታይን ሮም ስርወመንግስት ስብርብር አድርገው የቱርኮች የኢስላም ገባሪ አደረጉት ። ከሰልጁቆች ጎሳ #ከኪኒክ የሚመዘዘው የሰልጁቆቹ ጦር መሪ #አቲሲዝ_ቤይ ባይዛንታይኖችን አንኮታኩቶ ዳግም ቁድስ ነፃ አወጣት ። አላህ ዲኑን በማን እንደሚረዳው ይአጅባል ። ገና ከሰለሙ ጥቂት አመታትን ያስቆጠሩት ሰልጁቅ ቱርኮች የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን በሙሉ አስመልሰው ከቻይና እስከ ሮም ያሉ የኢስላም ጠላቶችን በጉልበቶቻቸው አንበረከኳቸው ።

፨ በሀያሎቹ ወራሪዎች ሞንጎሎች የሰልጁቆች የአባሲድና የኸዋርዚም ሙስሊም መንግስታቶች  ሲደመሰሱ አሁንም ዳግም አውሮፓዊያን ተባብረው " የመስቀል ጦርነት " በሙስሊሞች ላይ አወጁ ። ሁሉንም የአውሮፓ መንግስታት ባካተተውና በጳጳስ ክሊመንት በተባረከው በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች እንደ ቅጠል ረገፉ !! ኢየሩሳሌምን ( ቁድስ ) የሰው ደም ሀይቅ ሆኖ ተንጣለለባት ። ህፃናት አዛውንት ሳይሉ ፣ ሴት ደካማ ሳይሉ መስቀላዊያኑ ሁሉንም በሰይፋቸው አረዷቸው ። ቁድስም ዳግም በጭራቆች እጅ ገባች ።

፨ አሁን ደግሞ ቁድስን ዳግም ማስመለስ የአንድ በአሁኗ የኢራቋ ቲክሪት ከተማ የተወለደ ኩርዳዊ ሙጃሂድ ተራ ሆነ ። ያ ሙጃሂድ የሙጃሂድ ልጅ ሰላሁዲን አልአዩቢ ይባላል ።

ሰላሁዲን በሰልጁቅ የጦር መሪ በነበረው በኢማዱዲን ዘንኪ ልጅ በኑረዲን ዘንኪ አመራር ስር ሆኖ በወታደራዊ ክህሎት ተኮትኩቶ በኡለሞች ተርቢ ታንፆ አደገ ። አባቱ ሰላሁዲንን ከልጆች ጋር ሲጫወት ባገኘው ጊዜ ብድግ አደረገና ፍርጥ አደረገው ። እና ተቆጣው ሰደበው ። " እኔ አድገህ ቁድስን ታስመልሳለህ እያልኩ አንተ እዚህ አቧራ ታቦላለህ ?" አለው ። ሰላሁዲን አላለቀሰም ። ለምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና ።

ሰላሁዲን ቁድስን ነፃ ሳያወጣ በፊት ስቆ አያውቅም ተደስቶ አያውቅም ። ያ የአሏህ ወልይ በቱርኮች ጥምረት መላው የአውሮፓ መስቀላዊ ጦርን ደምስሶ ኢየሩሳሌም ( ቁድስን ) ዳግም ነፃ አወጣ ።

፨ ከዚያ በሗላ በግብፅ የነገሱት ቱርኮቹ ማምሉኮች ተረክበው ኢየሩሳሌምን ጠብቀው አቆዩ ።

፨ ከነርሱ በሗላ የአለማችን የምንጊዜውም ሀያሉ ኢምፓየር የሚሰኘው የኦቶማን ኺላፋ ( ደውለቱል ኡስማኒያ ) ቦታውን ተክቶ በየትኛውም የአለም ጫፍ ያለን የኢስላም ሉአላዊነት ሳያስደፍር ለ 500 አመታት ቀጥ አድርጎ ገዛ ። ያኔ እንኳንስ ቁድስንና ትሪፖሊን እንኳ ማጥቃት የኦቶማኖችን ጀሃነም ያስከትላል ። አውሮፓን በእንብርክኳ ያስኬዳት ፣ ሩሲያን ወገቧን የሰበራት ያ የኦቶማን ኺላፋ እሶከ ውድቀቱ መጨረሻ ድረስ ቁድስን መካንና መድናን ለጠላት አሳልፎ አልሰጠም ነበር !

፨ አሁን ቁድስ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላ በክርስቲያን_አይሁዳዊያን ጥምረት ስር ነች ። እነሆ ቁድስ ማንባት ከጀመረች ድፍን አንድ ክፍለዘመን ሊሞላት ነው ።

እና ከዚያ ሁሉ ጨለማ የወጣች ቁድስ አላህ አሁን ሌላ ሰላሁዲን ፣ ሌላ አቲሲዝ ቤይ ፣ ሌላ አልፕ አርስላንን አይልክላትም ብላችሁ ታስባላችሁ ??? በፍፁም አታስቡ !

ወድቆ መነሳት ፤ ጨለሞ መብራት የቁድስ ተፈጥሮዎች ናቸው !

ቁድስን አንድ ጊዜ አረቦች ፣ 3 ጊዜ ቱርኮች አንድ ጊዜ ኩርዶች ነፃ አውጥተዋታል ! አሁንስ እነማን የነፃነት ሰንደቁን ይዘው ቁድስን ነፃ ያወጡ ይሆን ??? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል !

ግና አትጠራጠሩ ቁድስ ነፃ ትወጣለች !!

#seid_mohammed_alhabeshiy

👉 t.me/Seidsocial

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group