📖የነቢዩሏህ_ሙሳ_አለይሂ_ሰላም_ታሪክ📖

                           ክፍል3

             🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹

አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ሙሳ ሆይ! ወደ ግብፅ ተመለስ። ፊርዐውንም ወሰን አልፏል" አለው።

ሙሳም፦" ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፡፡

ነገሬንም ለእኔ አግራልኝ፡፡

ከምላሴም መኮላተፍን ፍታልኝ።

ከቤተሰቦቼም ለእኔ ረዳትን አድርግልኝ፡፡

ሃሩንን ወንድሜን፡፡

ኅይሌን በእርሱ አበርታልኝ፡፡

በነገሬም አጋራው፡፡

በብዙ እናጠራህ ዘንድ፡፡

በብዙም እንድናወሳህ፡፡

አንተ በእኛ ነገር ዐዋቂ ነህና" አለው።

አላህም የሙሳን ፍላጎት እንዲሚያሳካለት ቃል ገባለት'ና ሙሳም ወደ ሚስቱ በመሄድ ወደ ግብፅ መሄድ እንዳለባቸው ነግሯት ከሚስቱ ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ጀመሩ።

      🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹

ግብፅ እንደገቡም ሙሳ የወንድሙን የሀሩን ቤት በመግባት ለሀሩን ሁሉንም ነገር ነገረው።ሀሩንም እጅጉን በመደሰት በሀሳቡ ተስማሙ።

በነጋታው ሙሳ እና ሀሩን ያለ ምንም ፍራቻ ወደ ፊርዐውን ቤተ መንግስት ዘልቀው ገቡ።ከዚያም ፊርዐውንን እንደተገናኙም ወደ አላህ እንዲመለስ'ና በኒ ኢስራኢሎችንም እንዳይበድል፤ ሙሳ እና ወንድሙ ሀሩንም የአላህ መልዕክተኞች መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።

ፊርዐውንም ከ10 አመት በፊት እቤቱ ይኖር የነበረውን ሙሳን በትኩረት ሲመለከት አወቀው'ና፦"አንተ ህፃን ሆነህ እቤቴ አላሳደግኩህም እንዴ!!! ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን? አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ"አለው

ሙሳም፦"ያን ግዜ ተሳስቼ ነው። ከዚያም እናንተ ትገድሉኛላችሁ ብዬ ሩቅ ሀገር ሸሸሁ። እዚያው ጌታዬም ጥበብን ሰጠኝ።ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ናት" አለው።

ፊርዐውንም፦" (ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው" አለው።

ሙሳም፦" የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)" አለው።

          🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹

ፊርዐውን ትንሽ ሳቀ'ና ወደ ዙሪያው ያሉትን ሰዎች እየተመለከተ፦"ሚለውን አትሰሙትም እንዴ!" አላቸው።

ሙሳም፦"የምሥራቅና የምዕራብ በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ታውቁ እንደኾናችሁ (እመኑበት)" አላቸው።

ፊርዐውንም፦"ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ" አለው።

ሙሳም፦"እኔ ከአላህ ዘንድ የተላክሁ ስለመሆኔ ማስረጃ ባመጣልህስ?" አለው።

ፊርዐውንም፦"እስቲ ማስረጃህን አምጣ እውነተኛ ከሆንክ" አለው።

ሙሳም ይህን ሲሰማ ብትሯን ጣላት፤ወዲያው ወደ እባብነት ተቀየረች።

ጣቱንም በብብቱ አስገብቶ የምታንፀባርቅ ሆና አወጣት።

       🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹

ፊርዐውን እችን ሲያይ፦" አሀ!!! ይህም ግልፅ ድግምት ነው።እንደውም እንዳንተ ያሉ ድግምተኞች በግዛቴ ብዙ ስላሉ ቀጠሮ እንያዝ'ና እንገናኝ ማን እንደሚያሸንፍ እናያለን"አለው።

ሙሳም በዚህ ተስማምቶ

ትልቅ ህዝባዊ በአል በሚከበርበት ቀን ቀጠሮ ተያይዘው ያን ቀን

በሰላም ተለያዩ።

ቀን ቀንን ወራት ወራትን እየተተካካ ሙሳ እና ፊርዐውን የያዙት ቀጠሮ ወቅቱን ጠብቆ መጣ።

ህዝቡ የዛሬዋን የቁርጥ ቀን ፍፃሜ ሊመለከት ለቁጥር አዳጋች ሆኖ በሰልፍ ተሰብስቧል።ድግምተኞችም እድሜ ልካቸውን ሲጠበቡበት የከረሙትን አስደናቂ ድግምት ይዘው ከሙሳ ሊፋለሙ ሰልፍ ይዘው ቁጭ ብለዋል። የድግምተኞች ብዛት 30,000(ሰላሳ ሺህ) ነበር።

(አስቡት በናታችሁ የድግምተኞቹ ቁጥር 30,000 ከሆነ የተመልካቹ ቁጥር ስንት ሊሆን ነው!!! ብቻ ትዕይንቱን በጭንቅላታችሁ ሳሉት)

         🌹•••✿❒🌹❒✿•••🌹

ተመልካቹም፣ድግምተኛውም፣ንጉሱም ሙሳም ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ድግምተኞቹ ቀስ ብለው ፊርዐውንን፦"ግን እኛ ካሸነፍን ምንድነው ሽልማታችን?" አሉት።

ፉርዐውንም፦"እኔ ዘንድ የቅርብ ባለሟል ትሆናላችሁ" አላቸው።

አሁን ጫወታው ሊጀመር ነው ፊርዐውን ዙፈኑ ላይ ተቀምጧል፣ሙሳ እና ወንድሙ ከአንድ ጎኑ ሲሆኖ ድግምተኞቹም ከአንድ ጎን ቆመዋል።ህዝቡ የትንቅንቁን ፍፃሚ ለማየት እጅጉን ጓግቷል።

#ኢንሻ_አላህ

                #ይቀጥላል..............

---------------------------------------------------------------

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ  ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇

-------------------------------------------------------------https://t.me/YereSulwedajoch_12

https://t.me/YereSulwedajoch_12

https://t.me/YereSulwedajoch_12

--------------------------------------------------------------

Send as a message
Share on my page
Share in the group