Translation is not possible.

ጥያቄ፦ጂኖች አጋንንት በሰዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላሉን? ከነሱ

የምንጠበቅበት መንገድስ ምንድነው?

መልስ፦ ጂኖች እስከመግደል ድረስ በሰዎች ላይ የተለያዩ አደጋዎችን

እንደሚያደርሱ ጥርጥር የለውም። ድንጋይ ሊወረውሩበት ይችላሉ። ሊያስፈራሩት

ይችላሉ። ሌሎች ችግሮችንም ሊያደርሱበት እንደሚችሉ በሀዲስም በተጨባጭ

ተረጋግጧል። ነቢዩ ( ﷺ ) በአንድ ዘመቻ ላይ እያሉ (በኽንደቅ ዘመቻ

ይመስለኛል) ለአንድ ሰሃባቸው ወደ ሚስቱ እንዲሄድ ፈቀዱለት። ወጣትና

ሙሽራ ነበርና። እቤቱ ሲደርስ ሚስቱ ደጃፍ ላይ ቆማ ነበር። ደጃፍ ላይ በመቆሟ

ተቆጣት። ግባና ታያለህ አለችው። ወደ ውስጥ ሲገባ እባብ ተጠቅልሎ ፍራሹ

ላይ ተቀምጧል። ጦር በእጁ ይዞ ነበርና በጦሩ ወጋው። እባቡ ሞተ። ወዲያው

ሰውየውም ሞተ። ማን ቀድሞ እንደሞተ እባቡ ወይስ ሰውየው አይታወቅም።

ጉዳዩ ለነቢዩ ( ﷺ ) ሲነገራቸው አብተርና ዙጡፈተይን የተባሉ እባቦች ሲቀሩ

በቤት ውስጥ የሚቀመጡ ጂንናን (የጂን እባቦች) እንዳይገደሉ ከለከሉ።

[ቡኻሪ]

ጂኖች በሰዎች ላይ ድንበር እንደሚያልፉና አደጋ እንደሚያደርሱባቸው ይህ

ማስረጃ ይሆናል። ተጨባጩ ሁኔታም ይህንኑ ያረጋግጣል። ሰው ሆና ወደ ሆነ

ቦታ ሄዶ ምንም ሰው ሳይኖር ድንጋይ እንደሚወረወርበት በሰፊው ይነገራል።

እሱን የሚያስፈራራ ድምፅና ኳኳታም ይሰማል። እንደዚሁም ጂን ወደ ሰው

አካልም ይገባል። አንድም አፍቅሮት ወይም ደግሞ ሊያሰቃየው ወይም በሌላ

ምክንያት። የሚከተለው የአላህ ቃል ይህንኑ ያመለክታል፦

ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺄْﻛُﻠُﻮﻥَ ﺍﻟﺮِّﺑَﺎ ﻟَﺎ ﻳَﻘُﻮﻣُﻮﻥَ ﺇِﻟَّﺎ ﻛَﻤَﺎ ﻳَﻘُﻮﻡُ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳَﺘَﺨَﺒَّﻄُﻪُ ﺍﻟﺸَّﻴْﻄَﺎﻥُ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤَﺲَِّ

“እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ነክቶት የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ)

እንደሚነሳ ብጤ እንጅ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡”

[አል-በቀራህ - 275]

ወደ ሰው አካል የገባው ጂን ከሰውየው ውስጥ ይናገራል። ሰውየው ላይ ቁርአን

የሚቀራበትን ሰው ያናግራል። ቁርአን የሚቀራው ሰው ጂኑ ወደ ሰውየው

እንዳይመለስም ቃል ያስገባዋል። እነዚህ ሁኔታዎች በሰዎች ዘንድ በስፋት

ታውቀዋል። ስለዚህ እንደ አየተል ኩርሲ ያሉና በሐዲስ የተዘገቡ ዚክሮችን

በመቅራት ሰው ከጂን ክፋት ሊጠበቅ ይችላል። አየተልኩርሲን በማታ የቀራን

ሰው አላህ ጠባቂ ያደርግለታል። እስከሚነጋ ድረስም ሸይጣን አይቀርበውም አላህ ይጠብቀን።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group