Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

መጥፎ ነኝ ወይስ ጥሩ ?

ሰው አልተረዳኝም እንጂ መጥፎ ነኝ ። ስያሜ አጥሮኝ እንጂ ከዚም በላይ ነኝ የሆዳቸው ዋሻ ጩኸቱ ቢጠናም ጆሮዬን ደፍኜ እጠግባለው ውርጩ የጠናባቸው የጥርሳቸው ግጭት ቢሰማኝም ደራርቤ እለብሳለው። ጎናቸው ከአስፋልቱ ዳር ደገፍ ያረጉትን ባይም በምናቤ በመስታወት ዙፋን ላይ ተቀምጬ አልማለው አንዳንዴ ግን አዝናለው ...

ድፍን ብሮችን ተሸክሜ ኪሴ ተነፍቶ ሆዱ የታጠፈ ቢለምነኝ መስጠት እየፈለኩ ዝርዝር ስለሌለኝ አላህ ይስጥልኝ ብዮ ዱዓ አረጋለው ጥሩ አይደለሁ? ዝርዝር ቢኖረኝ እኮ እሰጣለው

አንዳንዴም ከተረፈኝ አልያ የሚጠቅመኝ መስሎ ካልታየኝ እሰጣለው ፃዲቅ አይደለው?

ወደፊት ድሆችን አበላለሁ ትልቅ ምኞት አይደል አሁን ያለው ቢራብ ግድ አይሰጠኝም መሠለኝ! የድሀዎች መብዛት አጥብቆ ፈላጊ ሳልሆን አልቀርም እነሱ ባይኖሩ ባለፀጋነቴ ትዝ አይለኝም ህልም አልሜ በህልሜ ተመዝኜ ጥሩ አልባልም ነበር።

ሆኖም ግን ጥሩ ነኝ የተራበ ባይ ስሜቴ ይጎዳል ግን ቢጎዳም እራሴን በመረቅ እጠግናለው ለነሱ ብጨነቅም ጭንቀቴን በመዝናናት ለመርሳት እሞክራለው ያለኝን ከማካፈል ይልቅ ይህን ያጣ አለ በሚል ተረት አመስግኜ እተኛለው ። ጥሩ አይደለው 🌚

Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас