ደግነት
✍አንድ ጊዜ አባት ከቢሮ ድክም ብሎት ቤት ሲገባ ልጁ ሁለት ፖም ይዞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ አባት ፈገግ አለና ልጁን አንዱን ፖም እንዲሰጠዉ ጠየቀዉ፡፡ ይህን የሰማዉ ልጅ ሁለቱንም ፖሞች አንድ አንዴ ገመጥ ገመጥ አደረጋቸዉ፡፡
በዚህ ጊዜ አባት ተቆጣ... “አንተ ሆዳም! እንደዚህ ይደረጋል! አንዱ አይበቃህምና ነዉ ሁለቱንም ለመብላት የምትጣደፈዉ...!” እያለ የንዴት መትረየሱን አርከፈከፈዉ፡፡
ልጅ አዝኖ እንዲህ አለ “አባዬ እኔኮ ሁለቱንም የገመጥኩት ከሁለቱ የትኛዉ በጣም እንደሚጣፍጥ ለማወቅ ነዉ ...ይሄ በጣም ይጣፍጣል...ስለዚህ እንካ ላንተ! እኔ የቀረዉን ልብላ' ብሎት ለአባቱ የሚጣፍጠዉን ፖም ሰጠዉ፡፡ አባት እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡
አንዳንዴ ነገሮች ምንም ሳይገቡን መጮህ፣ መናደድና መቆጣት እንፈልጋለን፡፡ አንድን ነገር ዉጤቱን ገምተን ከምንጀምር ቀረብ ብለን ከመሰረቱ ብንረዳ የበለጠ መልካም ነዉ፡።