Translation is not possible.

በደል ሞልቶ ሲፈስ ፍልስጤን ሰማይ ስር

ሚስኪኖች ሲፈጁ በመሳሪያ ሀሩር

የህፃናት ተስፋ ሲሆን እንዳልነበር

አለም ፀጥ ብሎ ሲያይ ይሄን የግፍ ብትር

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኢስላምን ለማጥፋት ካፊር ሲተባበር

በጣም ያስገርማል የሙስሊሙ  ነገር

ልባችን ተደፍኖ በአዱንያዊ ፍቅር

ቁርዓንን  ትተን  በኮንሰርት ስንሰክር

ድናችንን ስንተው ተደፈርን በካፊር

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ህፃናት ሲፈጁ  በሙስሊምነታቸው

ደካሞች ሲያቅሱ በዳይ መቶባቸው

ሁሉም እጁን አጥፎ ቁጭ ብሎ ሲያቸው

አንተ አዛኙ ጌታ አላህ ሆይ እርዳቸው

ከአይሁድ ሙጅሪሞች አንተው ጠብቃቸው

ሁሉም ትቷቸዋል  መሸሻም የላቸው

ድሉን አጎናፅፈህ የበላይ አርጋቸው

የአለማቱ ጌታ አላህ ሆይ እርዳቸው

አሚን ያአላህ አሚን ያአላህ አሚን ያአላህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group