«አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.....!!»
⏠⏠
ክፍል ⓶
⏡⏡
⎘ እሷም ፈጠን በማለት “በአላህ ይሁንብኝ ይህ አይነት ቦታ አንተን የማይመጥን መሆኑ ፍጹም ጠፍቶኝ አይደለም እዚህ ቦታ ላይ ላናግርህ የፈለግኩት፡፡ ነገር ግን ማናገሬ ግድ ሆኖብኝ ነው የመጣሁት፡፡
⎘ በርግጥ እናንተ አላህን ፈሪ ሰዎች ከሉል እንደተሰራ ብርጭቆ ናችሁ፡፡ በጣም ጥቃቅን በሆኑ ነውሮች ዝናችሁ ይጎድፋል፡፡ በትንሽ ስህተቶች ክብራችሁ ይረግፋል፡፡
⎘ ባጭሩ ልነግርህ የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር መላው ሰውነቴ ሁሉ የአንተ ምርኮኛ ሆኗል፡፡ አካሌ በሙሉ አንተን ነው የሚያስበው፡፡ አንተን ማግኘት እሻለሁና እባክህ እዘንልኝ፡፡ ስቃዬን ተረዳኝ፤ ለራስህ እንደምታስበው ሁሉ ለኔም አስብልኝ የሚልን ያልተለመደ አስደንጋጭ ቃል አሰማችው፡፡
⎘ ያ ብዙ ጊዜውን በዒባዳ የሚያሳልፈው ወጣት በልጅቷ ጥያቄ ተደናግጦ ቀጥታ ወደ ቤቱ ገባ፡፡ ወዲያዉኑ ሶላት ለመስገድ በማሰብ መስገጃ ቦታው ላይ ቆመ፡፡ ነገር ግን እስከዛሬ በደንብ ሲቆጣጠረው የነበረውን ቀልቡን ዛሬ መቆጣጠር ተሳነው፡፡
⎘ አላሁ አክበር ሊል ሲሞክር ልቡ ይሸፍትበት ጀመር፡፡ ምን ብሎ መስገድ እንዳለበት ዘነጋ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀልቡን ዳግም በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ምን ማድረግ እንዳለበትአሰበ፡፡ ሃሳቡን እውን ለማድረግም የሆነችን ቁራጭ ወረቀት ያዘ፡፡ የሆኑ መልእክቶችን ጻፈበትና ከልጅቷ ጋር ወደ ተነጋገሩበት ቦታ አቀና፡፡
⎘ ወጣቷንም በቦታው ላይ ቆማ አገኛት፡፡ ከአጠገቧ ደረሰ፡፡ ምንም አይነት ወሬ ሳያወራት ወረቀቱን ሰጥቷት ብቻ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ አላህን ፈሪው ወጣት የጻፈው ደብዳቤ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
✍️ ይቀጥላል......
↷⇣⇣↶
https://t.me/https_Asselefya1