ጀግኖችን እንተዋወቅ ወደ ቀቤና
👉የኢማም ሀሰን እንጃሞ ታሪክ በጨለፍታ...
-----------------------------
የዚህን ጀግና ኢስላማዊ ሱልጧኔት መሪ #ኢማም_ሀሰን_እንጃሞን ሙሉ ታሪኩን ለማንበብና ለማጥናት ብፈልግም ስለሱ የሚተርክ መፀሀፍም ሆነ መፅሔት እስካሁን ለማግኘት አልቻልኩም።
ለቀጣይ ግን በተለይ ከቀቤና የወጡ ሙሁራኖቻችን የዚህን ጀግና ሰው ገድሉንና የፈፀመውን ጀብዱ ለኢስላም ያበረከተውን አስተዋፆ በመፀሀፍ አሳትመው ለንባብ እንደሚያበቁት ተስፋ አደርጋለሁ።
ይህ ጀግና #ኢማም የቀቤና ሱልጧን ከሚባል ይልቅ በኔ አረዳድ #የሐዲያ_የመጨረሻው_ኢስላሚክ ሱልጦኔት ከቀቤና የተገኘ ኮከብ የኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ኩራት ብለው እመርጣለሁ።
ምክንያቱም የዚህ ሰው የአመራር ጥበብና በማህበረሰቡ ውስጥ የፈጠረው ሀይማኖታዊይም ሆነ ማህበራዊ መስተጋብር በጥበብ የተሞላ ሐዲያን ጉራጌን ስልጤን ቀቤናን ሁሉንም አግባብቶና አስተባብሮ የመራ ጀግና ሰው ነው።
👉#የኢማም_ሀሰን_እንጃሞን የአመራር ጥበብ ለየት የሚያደርገው በሰዓቱ ለሁሉም ሙስሊሞች ደጀንነቱን ያንፀባረቀ ብቻ ሳይሆን በሱልጧኔቱ የስልጣን እርከኖች ስር ሀዲያን ፣ጉራጌን፣ስልጤን፣ቀቤናን ሌሎችንም ጭምር በየሴክተሩ በማዋቀር ለዘመናዊቷ ኢትዮጲያ ጉልህ ሚና እንደተጫወተ ነው።
እንደሚታወቀው የቀቤና ህዝብ #በኢማም_ሀሰን_እንጃሞ የመሪነት ሰዓትም ሆነ ከዚያ በፊት በነበረው የአኗኗር ዘየው በሀይማኖታዊ ፣በኢክኖሚያዊና በማህበራዊ መስተጋብር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበረው የማይካድ ሀቅ ነው።
የቀቤና ብሔረሰብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያዩ የሀይማኖታዊ እንቅስቃሴና በንግድ ስርዓት የተሳሰረ ከመሆኑም ባሻገር...ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢወች ተፈናቅለው የሚሰደዱ ሙስሊሞችን #የማይዘጋ_በሩን_ከፍቶ በመቀበልም ሚናው ከፍ ያለ እንደሆነ ይነገራል።
በተለይ ደግሞ በሰአቱ በእምነታቸው ብቻ #በአፄው_ስርዓት_ጭቆና የሚደርስበት #የወሎ ህዝብ ወደ ቀቤና በመሸሽ ምሽጋቸው ሆኖ የእምነት ወንድማማችነታቸውን አሳይተዋቸዋል ።
እንደዚሁም #ከአርሲ ወደ ቀቤና ብሎም በተለያዩ ጉዳይች የተሰደዱ ሙስሊሞችን በፍቅር ተቀብሎ ያስተናገደ ጀግና መሆኑን ልዩ ያደርገዋል።
👉#ኢማም_ሐሰን_እንጃሞ በዘመኑ
ሙስሊም ሰራዊቶችን ያዋቀረ እና ኢስላማዊ ታሪኩን አንድ እርምጃ ከፍ እንዳደረገ ከመነገሩም በላይ👉በጉራጌ ዞን በሰዓቱ #ምሁር እና #አክሊል የተባሉ ሁለቱ ቦታወች ብቻ ሲቀሩ ሁሉንም #በኢስሊም ሀይማኖት ስር እንዳጣመረውና ሰላምን ፍትህንና እኩልነትን እንዳሰፈነ ይነገራል።
በተለይ #ጉመር_ወረዳ ላይ አስደናቂና ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ፈፅሟል።
በዚያ አካባቢ ማለት በጉመር ወረዳ #መስጂድ የሚባል ስያሜ ያለው ቦታ አለ ይህ ቦታ የአቶ #በርከፈት_ውጅሌ የሚባሉ ሰው ቦታ ሲሆን እሳቸውም ወንድሞቻቸውም ሙሉ ቤተሰባቸው ኢስላምን ከተቀበሉ በኋላ..ቦታው የሙስሊሞች ሀብት ሆኖ ዛሬ ላይ #ኢስላሚክ_ዩኒቨርሲቲ እየተቋቋመበት እነሰደሆነ ሰምቻለሁ።
ሙስሊሞች ሆይ
ከተውሒድ ላይ ከማተኮራችን ባሻገር ታሪካችንን እንወቅ እናንንብብ እላለሁ።
✍️ኑረዲን አል አረቢ
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.