Translation is not possible.

#ሽማግሌ__ነው

.

በህይወቱ ያሳለፋቸውን ምኞቶቹን ሲያወጋ እንዲህ ይላል:— "አላህ መልካም

ትዳር እንዲሰጠኝ ተመኘሁ። ሆኖልኝ መልካም ሴት አገባሁ።

.

…ነገርግን ትዳር ያለ ልጅ አይሞቅምና አላህ ልጆች እንዲሰጠኝ ተመኘሁ።

ህልሜም እውን ሆነ። ልጆች ተወለዱልኝ።

.

…ነገርግን ብዙም ሳልቆይ የቤቴ ጥበት ሰለቸኝ። ጋርደን ያለው ሰፊ ቤት

እንዲኖረኝ ተመኘሁ። ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ተሳካልኝ። የተመኘሁትን ቤት

ገነባሁ።

.

…ነገርግን አሁን ደግሞ ልጆቼ ደርሰዋል። ስለዚህ ወግ መዕረጋቸውን ለማየት

ተመኘሁ። ውጥኔ ተሳካና አገቡ።

.

…ነገርግን ሥራ ሰልችቶኛል። የህይወትን ግብግብን መወጣት አልቻልኩም።

ስለዚህ ጡረተኛ በመሆን እረፍት ማግኘት ተመኘሁ። ተሳካልኝ።

.

…ነገርግን አሁን ቀድሞ እንደነበርኩት ብቸኛ ሆኛለሁ። እንደውም ከቀድሞው

የሚከፋው ድሮ ወደ ህይወት እየቀረብኩ፣ ኑሮ እየመሰረትኩ ነበር። አሁንስ?!

ለጉዞ እየተሰናዳው ሞቴን እየጠበኩኝ። ወደፊት ይመጣል ብዬ የምጠብቀው

ምንም ዓለማዊ ነገር የለም።

.

…ነገርግን አሁንም መመኘት አላቆምኩም።…ቁርኣን መሐፈዝ ተመኘሁ። ነገርግን

የማስታወስ ችሎታዬ ተዳክሟል። መጾም ተመኘሁ። ነገርግን ጤናዬ ተቃውሷል።

አልቻልኩም። ለሊት መስገድ ተመኘሁ። ነገርግን እግሬ ሊሸከመኝ

አልተቻለውም።…"

.

#ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል:— "አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት

ተጠቀምባቸው:

— ወጣትነትህን ከእርጅና በፊት

— ከህመምህ በፊት ጤናህን

— ኃብትህን ከድህነትህ በፊት

— በሥራ ከመጠመድህ በፊት ትርፍ ጊዜህን

—ከመሞትህ በፊት ሕይወትህን"

.

የቀን ፕሮግራምህ ላይ:—

/ በጧት ከሥራ በፊት ሁለት ረከዐ አዱሐ ከሌለ…

/ ምንም ያህል ቢያንስም የምትችለውን ያህል የቁርኣን ዊርድ ከሌለ…

/ ከዒሻእ በኋላ ከፈጅር ሶላት በፊት ዊትር ከሌለ…

/ መልካም ነግግር ከሌለ…

/ የጌታን ቁጣ የሚያበርድ ሶደቃ ከሌለ…

/ ከአላህ በቀር ማንም የማያውቀው ድብቅ ስራ ከሌለ…

.

… ሕይወት ምን ጣዕም አለው!?

.

ኢላሂ ጀነትህን ስጠን ከእሳት ጠብቀን። ያማረ ህይወትና የደጋጎቹን ሞት ለግሰን!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group