Qumuqta qilghuchi yo'q.

አትዘን /አትጨነቅ📌

🔺#ሀዘን?ቀልብን ያደክማል🔺ቆራጥነትን ያጠፋል🔺ፍላጎትን ይቀይራል

♻️ ለሸይጧን ከሙእሚን ማዘን የበለጠ የሚያስደስተው ነገር የለም።

✅ አትዘን አትጨነቅ አላህ ላንተ ያለውና የፃፈው ጊ ዜው ቢዘገይ እንጂ የትም አይሄድም።

✅ ያንተ መጨነቅና መጠበብ የራቀን አያቀርብም የቀረበውንም አያርቅም። ሀዘን ትካዜህ አላህ ላንተ ከቀደረው ውጪ ምንም ሊያመጣልህ አይችልም።

✅ ስታገኝም ስታጣ፣ ስትደሰትም ስትከፋ በሁሉ ሁኔታህ  "አልሀምዱሊላህ" በማለት አመስጋኝ ባሪያ በመሆን በሀሴት በደስታ ማሳለፍ እንጂ የምን መጨነቅ ነው❗️

✅ ማንኛውም ሙሲባ ወይም ችግር ባጋጠመህ ጊዜ ከዙሪያህ አይዞህ ባይ ስላጣህ፣ ሀብት ወይም ዘመድ በአጠቃላይ ችግርህ የምታወያየው አለኝ የምትለው ስለሌለህ አትጨነቅ አትከፋ። የነገራቶች ሁሉ ባለቤት የሆነው አላህ ከምንምና ከማንም በላይ ላንተ ቅርብ ነውና ማዘኑን ትተህ ወደሱ ዙር። የዛኔ ባላሰብከው ሰበብ

🔺ሀዘንህ ወደ ደስታ

🔺ጭንቀትህ ወደ ሰላም

🔺መረበሽህ ወደ እርጋታ ይቀይርልሀልና።

➝➀ ምስጋና ማድረስን ከወፈቀህ

የመልካም ነገርን ጭማሪን አይከለክልህም

➝➁ ዱአ ማድረግ ከወፈቀህ

      ምላሹን  አይነፍግህም

➝➂ ኢስቲግፋር ማድረግን ከወፈቀህ

        ምህረቱን  አይከለክልህም

➝➃ ተውባ መግባትን ከወፈቀህ

         ተቀባይነትን አይከለክልህም

➝➄ ሰደቃ መስጠትን ከወፈቀህ

         አጅሩን አይከለክልህም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group