Translation is not possible.

ሀማስና እስራኤል ሰሜን ጋዛ ላይ ከባድ ውጊያ እየተዋጉ ነው ። የእስራኤል ጦር ለመግባት ሀማስ ላለማስገባት የሚደረግ የሞት ሽረት ጦርነት !!

በጦርነቱ ሀማስ በርካታ የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን አሳውቋል በርካታ ታንኮችንም አውድሟል ። እስራኤል በበኩሏ በሰጠቺው መግለጫ አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንኗ በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰሉን አስታውቃለች ። ኔታኒያሁ ጦርነቱ እጅግ ፈታኝ ነው ረጅም ጊዜም ይወስዳል ብለዋል ።

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሰይድ ኢብራሂም ረኢሲ ይህ የእስራኤል ጦር ዛሬ የደረሰበት ሽንፈት ከመጀመሪያው የሀማስ ጥቃት በሗላ ሁለተኛው ድል ነው ብለዋል ። እስራኤል በበኩሏ ለደረሰባት ወታደራዊ ኪሳራ ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች ። በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ስምሪት የኢራን እጅ ነው ሀማስን ያፈረጠመው በማለት እየወቀሰች ነው ።

ጦርነቱ በርትቷል ጫናውም እስራኤል ላይ አርፏል ። የእስራኤል ባለስልጣናት ተከፋፍለው ሲወቃቀሱ ውለዋል ። ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ለዚህ የእስራኤል መዋረድ የሀገሪቱን ጦር ተጠያቂ የሚያደርግ ፅሁፍ ትዊተር ላይ ለጥፈው ውግዘት ሲበዛባቸው አጥፍተውታል ።

ትግሉ ይረዝም ይሆናል እንጅ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ይጠይቅ ይሆናል እንጅ ለፍልስጤማውያን አይሸነፉም !!

Send as a message
Share on my page
Share in the group