Translation is not possible.

በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና እጅግ በጣም ሩህ ሩህ በሆነው

አሏህ (ሱ ወ) ለኛ ለሰው ልጆች አደራ ካለበት ወሳኝ ጉዳዮች መሀከል የወላጅ ሀቅ አንደኛው ነው ፡፡

የወላጅ ሀቅ እጅግ ከባድ ከመሆኑ ጋር ዛሬ በአብዛኞቻችን በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከተረሱትና ከተዘነጉት ግዴታዎች መካከል የግንባር ቀደሙን ቦታ ይዞ ይገኛል ቢባል ማጋነን አይሆንም ።

ኢስላም ለወላጆች የሰጠውን ከፍተኛ ቦታ እኛ ሙስሊሞች ጋር እንደ ተራ ነገር ተቆጥሮ ባለበት በዚህ ዘመን ወላጆቹን ተጠቅሞ እነርሱን በማገልገል የጀነት በሩን ያንኳኳ ምንኛ ታደለ ! አሏህ ይጠብቀንና እነርሱን አሳዝኖ ደግሞ ጀነት መግባት ያልቻለ ምንኛ ከሰረ ?

አሏህ እንዲህ ይላል

ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው ( አል አህቃፍ )

በወላጅ ጉዳይ አደራ ያለው አሏህ ሆኖ ሳለ የአሏህን አደራ የበላን ስንቶቻችን እንሆን ?

በቂያማ ቀን አሏህ (ሱ.ወ) ከማያያቸው እና ከማያናግራቸው አራት ሰዎች መካከል የመጀመሪያው ወላጆቹን በዳይ የሆነውን ነው ሲሉ የአሏህ መልአክተኛ (ሰ ዐ ወ) ተናግረዋል !

በሌላ ሀዲስ የጀነትን ሽታ ( ጀነትን ሳይሆን ሽታዋን )ከማያገኙት ሰዎች መካከል ለወላጆቹን በጎ የማይውል እንደሆነ መናገራቸው የሚታወስ ነው ፡፡

ይህ ከሆነ ታዲያ መመለሻችን የሆነው አኼራ ምን ይጠብቀን ይሆን ? በወላጆቻችን ምክንያት እነርሱን አስደስተን ጀነት ወይስ እነርሱን አስከፍተንና አሳዝነን የአሏህ ቁጣ ? ምርጫው የኛ ነው ፡፡

በአጠቃላይ ወላጅን ማስከፉቱ ይቅርና "ኡፍ" ልንላቸው እንደማይገባ ቁርዓን አስጠቅቆናል !

Send as a message
Share on my page
Share in the group