Translation is not possible.

ኢትዮጲያ በፍልስጤም ጉዳይ አስቸኳይ ምግብ ይግባ አይግባ ለሚለው ውሳኔ በድምፀ ተዓቅቦ አሳለፈች !

ተመድ በጠራው ስብሰባ ላይ ሀገራችን ኢትዮጲያ የፍልስጤም ጉዳይን በተመለከተ 120 ሀገራት ምግብ በአስቸኳይ ይግባ ብለው ድምፅ ሲሰጡ ኢትዮጲያ በዝምታ አልፋዋለች :-D

ባለፈው ጁሙዓ ፍልስጤምን እና እስራኤልን በተመለከተ በተባበሩት መንግስት በተመድ ስብሰባ ተደርጎ ነበር

የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦

- በ120 ድጋፍ፣

- በ14 ተቃውሞ

- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።

ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group