Translation is not possible.

አርብ ከሰዓት በኃላ በተደወለ ስልክ ከስር የምትመለከቷቸው ወንድሞችን መታሰራቸውን ሰምቼ ነበር ። ፌስቡክ ላይም እንዲፈቱ የተቻለንን ለማድረግ አስበን ኡስታዝ አቡበከር ጉዳዩ ላይ እንደገባ ስንሰማ ያለምንም ጥርጣሬ እንደሚያስፈታቸው እርግጠኛ ሆነን ዝም አልን ። የሆነውም ይሄ ነው ።

በ16/02/16 በቤተል ተቅዋ መስጂድ ለፍልስጤም ላይ እየደረሰ ባለው የግፍ ጥቃት ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር ። በኃላ በቦታው የነበሩ ሰዎች ከተበተኑ በኃላ በሲቢል ፖሊስ በመከታተል እነዚህን ወንድሞች ወደ እስር ቤት ይዘዋቸው ሄደው ነበር ። በሰዓቱ እስር ላይ መሆናቸውን እና ከሚመለከተው አካል ጋር አውርቶ የታሰሩበት ጉዳይ አግባብ እንዳልሆነ የሚያስረዳላቸው የተለያዩ ሰዎች ጋር ቢደወልም ለስልካቸው አፋጣኝ ምላሽ የሰጠው ግን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ነው ። ጉዳዩ ከተፈጠረ ሰዓት አንስቶ ብቻውን እንደተቋም ተንቀሳቅሶ ለቤታቸው እንዲበቁ አድርጓል ።

ትላንትም ዛሬም ሙስሊሙ ላይ በሚደርሰው በደልም ሆነ አላግባብ እንግልት ከፊት ሆኖ ነገሮችን ሲፈታ አይተናል ። ዛሬም ያደረገው ይሄንኑ ነው ።

Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ. አላህ በአፊያ በክብር ያቆይህ ...!

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group