Translation is not possible.

«የእስራኤል ሀገረ-መንግስት የቆመው በደም እና እንባ ላይ ነው!

ሙሉ ታሪክ እና እውነታ ሳናውቅ አንፍረድ።

የእስራኤል አገረ-መንግስት(the Jewish state) በደም እና እንባ ላይ የቆመች ናት። የዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ከፍታችሁ ብትመለከቱ ስለ ፍልፄም ህዝብ መከራ እና ስቆቃ የሚያወሩት በጣም ጥቂት ነው። ምክንያቱም እስራኤል በወንጀል ላይ ወንጀል፣ በበደል ላይ በደል እየፈፈፀመች እራሷን ሁል ጊዜው እንደ ብቸኛ ተበዳይ ስለምታቀርቅ! ዘመናዊ የአፓርታይድ ስርዓት ዘርግታ፣ የፍልፄም ዜጎችን ከሰው በታች እየቆጠረች( subhuman) ጎፈሬዋን አበጥራ የአለም ድግስ ላይ ትቀርባለች። በፍልፄም ህዝብ ላይ ከተፈፀመው ያገጠጠ ግፎች መካከል በጥቂቱ:-

-ከ3.5 ሚልዮን በላይ ህዝብ ከራሱ መሬት ተፈናቅሎ፣ በገዛ አገሩ እንደ ስደተኛ እንዲኖር ተደርጓል፣

-የአይሁድ አገር ለመመስረት የዘር ማፅዳት ፖሊሲ ላለፉት 75 ዓመታት ሲፈፀም ቆይቷል።

-የጋዛ ፀርጥ ላለፉት 18 ዓመታት በከበባ ውስጥ እየኖረ ነው፣

-የተባበሩት መንግሥታት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የአለምአቀፍ ወንጀሎች በእስራኤል እየተፈፀመ መሆኑን በየጊዜው ቢያሳስቡም የምዕራቡ ዓለም ጆሮ ዳባ ብሏል፣

-የፍልፄም ህጋዊ ግዛት( በ1947 በተመድ የተሰመረው) በየወቅቱ እንደ ፌስታል እየሟሸሸ የበሬ ግንባር አክሏል፣

-በራሳቸው ግዛት ላይ እንኳን በየእርምጃው ፍተሻ አለ፣ ፍልፄሞች የማይረግጡት ጎዳና አለ( ለምሳሌ ሄብሮን ግዛት ውስጥ ተመልከቱ)፣

-የፍልፄም ህዝብ ማንነት እና ታሪክ ተነፍጓል፤ ነገር ግን የምዕራቡ ዓለም ለሌላው የራስን ዕድል በራስ መወሰን ብሎ ይሰብካል፣

-እስራኤል የጉልበተኛ አስተዳዳሪ (occupying force) ሆኖ እንኳን ትንሹን የዓለም አቀፍ ግዴታ አለተወጣም፣

-የሰሞኑን ሁኔታ ብቻ ብንመለከት እንኳን ሐማስ ካደረሰው ጥቃት በኋላ እስራኤል የወሰደችው እርምጃ የተገኘውን ፍልፄማዊ የማጨድ ፖሊሲ ነው። እሁድ ጦርነት አውጀናል አሉ፣ ቀጥለው ትናንት ሙሉበሙሉ ጋዛ ከበባ ውስጥ እንድትገባ ታዘዘ(complete siege of Gaza)፣ ይሄንን ያደረጉት ደግሞ ፍልፄሞች እንሰሳ ስለሆኑ ነው አለ የእስራኤል የመከላከያ ሚንስትር። ይሄ ሁሉ እየሆነ፣ አሰቃቂ የዓለምአቀፍ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ሳለ፣ ምዕራባውያን በአንድ እግር ቆመው ለሚስኪኗ እስራኤል ድረሱ እያሉ ነው።

በታሪክ የመገፋትን ስሜት የሚያውቅ ሌላውን አይገፋም ይባል ነበር፤ ይሄ ግን ለአይሁዳዊያን እስራኤል አይሰራም!

አየህ፣ ይህች ዓለም የግብዞች ጥርቅ፣ ጉልበተኞች የሚከበሩባት፣ ድሃ የሚበደልባት ሆናለች። እራሱ በድሎ እራሱ የሚያለቅስበት ሜዳ!

ከማንም ጋር አትለጠፍ፣ አጣርተህ ከተበደለው ጋር ተሰለፍ፣ ከፍትህ ጋር ብቻ ቁም! በሀይማኖት ምክንያት አታሽቃብጥ!!!

*የግርጌ ማስታወሻ: እስራኤል የክርስትናም ሆነ የእስልምና ጠበቃ አይደለችም፣ የአይሁድ ምድር ናት።»

Send as a message
Share on my page
Share in the group