siraju din

is feeling Celebrate
1 year Translate
Translation is not possible.

እውነታው ይነገር!

-----

አፈንዲ ሙተቂ

------

የአውሮጳ ሀገራት እና አሜሪካ ለ1900 ዓመታት አይሁዶችን ሲወቁ፣ ሲያስፈራሩ፣ ሲዘልፉ፣ ሲጨቁኑ፣ ሲያሰቃዩ፣ ሲዘርፉ፣ ሲገድሉ እና ሲገርፉ ነበር። አይሁዶች የጭካኔ እና የስግብግብነት ምልክት ተደርገው ሲጻፍባቸው ነበር።

=> ዊሊያም ሼክስፒር በጻፈው "የቬኒሱ ነጋዴ" ውስጥ "ገንዘቤን በጊዜ ካልከፈልከኝ ከሰውነትህ አንድ ኪሎ ስጋ ቆርጬ እወስዳለሁ" ብሎ ገንዘብ የሚያበድረው ሻይሎክ የተባለ አራጣ አበዳሪ አይሁድ ሆኖ ነው የተቀረጸው።

=> "ጄኔራል ድሬይፉ" የተባለው አይሁዳዊ የፈረንሳይ ጄኔራል ምንም ሳያጠፋ "የፈረንሳይን ወታደራዊ ደህንነት መረጃ ለጀርመን አሳልፈህ ሽጠሃል"በሚል ተወንጅሎ የደረሰበት መከራ ዓለምን አነጋግሮ ነበር።

=> የናዚ ፓርቲ በጀርመን ስልጣን ሲይዝ የአይሁዶችን ንብረት ከመቀማት ጀምሮ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን በእቶን እሳት አቃጥሏል።

------

የምዕራቡ ዓለም አይሁዶችን በሚያሰቃይበት እና በሚፈጅበት የመከራ ዘመን በሐዘኔታ አቅርቦ ያስጠለለው የሙስሊሙ ዓለም ነው። በተለይም የኦቶማን ቱርኮች ኢምፓየር በ15ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ መርከቦችን በማሰማራት የስፔን አይሁዶችን ከግድያ ለማትረፍ ጥሯል።

በዛሬው ዘመን ግን ታሪክ ተገለባብጦ በወንጀለኛነቱ የሚታወቀው የምዕራቡ ዓለም የአይሁድ ደጋፊ መስሎ ይታያል። አውሮጳዊያን በአይሁዶች ላይ ለሰሩት ግፍ ዕዳውን የሚከፍለው መከረኛው የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆኗል።

------

ይስሐቅ ራቢን እና ያሲር አራፋት በ1993 በኦስሎ የሰላም ስምምነት ሲፈራረሙ ነፃ እና ሉዓላዊት ፍልስጥኤም በአስር ዓመት ውስጥ እንደምትመሠረት ተግባብተው ነበር። ይስሐቅ ራቢን ስምምነቱን ፈርሞ አንድ ዓመት ሳይሞላው ተገደለ። የሰላም ስምምነቱን ያፈራረመው የአሜሪካው ቢል ክሊንተን በጀመረው ጎዳና እንዳይቀጥል ለማድረግ ሲሉ "ሞኒካ ሊዊንስኪ" የተባለች ዱርዬ ልከውባት አሳሳቱትና ስራውን እንዳይሰራ ክፉኛ አወኩት። ክሊንተን በመጨረሻዋ ሰዓት አራፋትንና ኢሁድ ባራክን ለማገናኘት ያደረገውንም ጥረት አከሸፉበት። የኦስሎ የሰላም ስምምነትም ሳይተገበር ሃያ ዓመት አለፈው። በመሃሉ እስራኤል የኒውክለር ቦምብ ታጣቂ ሆና ብቅ አለች።

-------

እውነተኛ የፍርድ ተቋም ቢኖር የምዕራቡ በፍልስጥኤማዊያን ላይ ለተሰራው የ75 ዓመት ግፍ ከእስራኤል በላይ ተጠያቂ ይሆን ነበር።

#palestineshallbefree

Send as a message
Share on my page
Share in the group