Translation is not possible.

[[[ የትኛው ስራ ነው በላጩ ]]]

{ በባህር ዳርቻ አንድ ለሊትን(በአላህ መንገድ ላይ) መጠበቅ አንድ ሰው በቤተሰቡ ውስጥ ለአንድሺ ቀናቶች ከሚሰራው(ኢባዳ) በላጭ ነው} በሚለው ሀዲስ ላይ ኢብን ተይሚያህ ረሂመሁላህ እንዲህ ተብሎ ተጠይቀው መልሰዋል

ጠያቂ፦ በመካ በበይተል መቅዲስ እና በመዲነተ ነበዊያ በኢባዳ ኒያ እና ከአላህ ጋር ለመገናኘት በዛ ከመሆን እና በደሚይጣ(በግብፅ የሚገኝ ከተማ) ፣ በእክንድሪያ(ግብፅ የሚገኝ ከተማ) እና በጠራቡለስ(ትሪፓሊ) በሪባጥ ኒያ ከመቀመጥ ከሁለቱ የትኛው በላጭ ነው?

መልስ፦ በሙስሊም ጦር ቦታዎች እንደ ሻም እና ግብፅ ጦር ቦታዎች (በሪባጥ) መቆም ሶስቱን መስጂዶች ከመጎብኘት ይበልጣል።

በዚህም ላይ በእውቀት ባለቤቶች መካከል ልዩነት ስለመኖሩ አላቅም። ይህንን ያስቀመጠ አንድም አኢማ የለም።

በዚህም ሪባጥ ከጅሀድ ክፍል ውስጥ አንዱ ሲሆን ጉብኝቱ ደግሞ ዋና አላማው በሀጅ ጉዳይ ላይ ነው። አላህ እንዳለው

[ ካእባ ጎብኚዎችን ማጠጣት እና የተከበረውን መስጂድ መስራትን በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድ እንደታገለ ሰው(እምነትና ትግል) አደረጋችሁን? አላህ ዘንድ አይስተካከሉም]

በሰሂህ እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የትኛው ስራ ነው በላጩ ተብለው ተጠይቀው እሳቸውም "በአላህና በመልእክተኛው ማመን" አሉ ከዛስ ሲባሉ "ጅሀድ ፊሰቢሊላህ" አሉ ከዛስ ሲባሉ"ሀጅ መብሩር" አሉ።

በሌላ ዘገባ [ በአላህ መንገድ ላይ ዘመቻ መውጣት ከሰባት ሀጆች የበለጠ ነው] ብለዋል።

ሙስሊም በሰሂሀቸው ላይ ባስቀመጡት ከሰልማን አልፋሪሲ በተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

[ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ የአንድ ቀንና የአንድ ለሊት ጥበቃ ከአንድ ወር ፃምና ለይል መቆም የተሻለ ነው። ቢሞት(ሙራቢጥ ሆኖ እያለ ሪባጥ ላይ ቢገደል) ሲሰራ በነበረው መልካም ነገር ሁሉ ምንዳ ማግኘቱን ይቀጥላል። ለቤተሰቡ ሲመጣለት የነበረው ሪዝቅም አይቋረጥበትም። ከቀብር ውስጥ ፈታኞችም ይጠበቃል ]

ከኡስማን በተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል [ በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን ሪባጥ ማድረግ በሌላ ቦታ ከሚደረግ አንድ ሺ ቀን በላጭ ነው ]

ይህንንም ንግግር ኡስማን ረዲየላሁ አንሁ ሱናውን ለማድረስ ሲለ በአላህ መልእክተኛ ሚንበር ላይ ተናግረውታል

አቡ ሁረይራም እንዲህ ብለዋል፦[ በአላህ መንገድ ላይ አንድ ለሊትን ሪባጥ ማድረግ ሀጀረል አስወድ ጋር ለይለተል ቀድርን ከመቆም እኔ ዘንድ የበለጠ ነው]

የሪባጥ እና በአላህ መንገድ ላይ ጥበቃ የማድረግ ፈድሎች ብዙ ናቸው ይህ ወረቀት አይበቃውም። አላሁ አእለም

Send as a message
Share on my page
Share in the group