አልጀዚራ የቀጥታ ስርጭት ከማታ ጀምሮ አዳሩን በሰበር ዜና ያሰራጫቸውን ዋናዋና ዜናዎች መራርጬ ወደ አማርኛ መልሼላችዃለሁ…መልካም ንባብ!
▶️የአልቀሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ #አቡ_ዑበይዳህ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
“ሰላም ለነዚያ ለጌታቸው ካልሆነ በቀር ጀርባቸውን በማያጎንብሱት ላይ ይሁን!” በማለት የጀመረው ሙጃሂድ አቡ ዑበይዳህ፣“ጥቅምት 7 ቀን የጠላት ምሽጎች እንደ ሸረሪት ድር ሲፈርሱ እና አንድ ተዋጊያችን ሶስት የጠላት ታንኮችን ሲያወድም የአሏህ እርዳታ በአይናችን አይተናል!”በማለት አክሏል።
▶️“ጠላት በመኖሪያ ሕንፃዎችና በሆስፒታሎች ላይ ማነጣጠሩ ውርደትንና ሽንፈትን እንጂ ሌላን አያመላክትም” ያለው የሙጃሂዶቹ ቃል አቀባይ ሙጃሂድ አቡዑበይዳህ አያይዞም
▶️“የጠላት ወታደራዊ እና የስለላ የበላይነት አለ የሚባልበት ዘመን አብቅቷል!እናም የጽዮናዊት የሽንፈት ዘመን ጀምሯል!”በማለት በኦክቶበር 7 ላይ ያስመዘገቡት ድል ትልቅ ሞራል እንደፈጠረላቸውና እስከመጨረሻው ለመዋጋት መወሰናቸውን እወቁልን ብሏል!ጠላት ከጠበቀው በላይ ሽንፈትን እንዲቀምስ እናደርጋለን በማለትም ዝቷል የጀግኖቹ የሚድያ ሀላፊ ጀግናው ሙጃሂድ #አቡ_ዑበይዳህ!
▶️የሐማስ ምክትል ሊቀመንበር ሳሌህ አል አሮሪ የፍልስጤም ተቃውሞ አሁንም የውጊያውን ሂደት እየተቆጣጠረ ነው እናም በዚህ ጦርነት ግቦቹን ከማሳካት ወደኋላ አይልም ብለዋል።
یَـٰلَیۡتَنِی كُنتُ مَعَهُمۡ فَأَفُوزَ فَوۡزًا عَظِیمࣰا
▶️ለአረብ መሪዎች ጠንከር ያለ መልእክት ያስተላለፈው አቡ ዑበይዳህ“እኛ የእናንተን ታንክ፣አውሮፕላንና ወታደር አንፈልግም…ቀቅላችሁ ብሉት አይነት…ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ ትንሽዬ ሀሞት ካላችሁ የእርዳታ ተሽከርካሪዎችን እንዲታንቀሳቅሱ እንጠይቃለን!”በማለት በአረቦች ደዩስነትና ተወዳዳሪ የሌለው ፍርሐት በጣም እንደተበሳጩባቸውና እንዳፈሩባቸው በሚያመላክት ንግግር ክፉኛ ተችቷቸዋል!
“እየሩሳሌምን ነፃ ለማውጣት እና የሀገሪቱን ክብር ለማደስ በታሪካችን ወሳኝ ጦርነት ገጥሞናል!”ያለው የጀግኖቹ ቃል አቀባይ ጀግናው ሙጃሂድ አቡዑበይዳህ
▶️“የፍልስጤም እስረኞች ከየእስር ቤቱ ካልተፈቱ በስተቀር የጠላት እስረኞችን መፍታት አይታሰብም!ጠላት የፍልስጢን እስረኞችን በአንድ ጊዜ ለመፍታት ከፈለገ እኛም ተዘጋጅተናል”በማለት ሰብኣዊ እርዳታ እንድገባ በሚል የፅዮናዊት እስረኞችን መልቀቅ ትክክልና ተገቢ እንዳልሆነ በገደምዳሜው ጠቁሟል!
▶️በጋዛ የሚገኘው የሃማስ እንቅስቃሴ ሃላፊ ያህያ ሲንዋር ለአል-አቅሳ ቲቪ እንደተናገሩት በተቃውሞው የተያዙ እስረኞችን በሙሉ ለመልቀቅ በወረራ የተያዙ እስረኞችን መፍታትን የሚያካትት የልውውጥ ስምምነት ለመደምደም ተዘጋጅተናል በማለት የአቡዑበይዳህን ንግግር ደግመዋል።
▶️የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ እስረኞቹን አስመልክቶ ለሐማስ መግለጫ በሰጠው መልስ“ሃማስ በእስራኤላውያን ላይ ጫና ለመፍጠር የስነ ልቦና ጦርነት እያካሄደ ነው!”ብሏል።
▶️በእየሩሳሌም የሚገኘው የእስረኞች ክለብ ሃላፊ ለአልጀዚራ ቀጥታ እንደተናገሩት ከጥቅምት 7 በፊት በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩት እስረኞች ቁጥር 5,200 ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 400 ህጻናት እና 32 ሴት እስረኞች ይገኙበታል።
▶️ትላንት ቅዳሜ በብዙ መቶሺህዎች በተገኙበት የኢስታንቡል ሰልፍ ላይ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጠንከር ያሉ ንግግሮችን በመናገራቸውና ሀማስ የነፃነት ታጋይ እንጅ ፈፅሞ አሸባሪ አይደለም…በዚህ አቋማችን እስራኤል ብትቀየምም የራሷ ጉዳይ…እንዳውም አሸባሪዋ ራሷ ፅዮናዊቷ መሆኗን ለዓለም ህዝብ እናሳውቃለን…በማለት በተናገሩት ንግግር ምክናየት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቱርክ ጋር ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ እና ግንኙነት እንደገና እንገመግማለን!”በማለት ቲውተር(X)ላይ ፅፏል።ማን ሊጎዳ?
▶️በጋዛ ውስጥ የመንግስት ሚዲያ ኃላፊ“ፍልስጤማውያን ለወረራ ማስፈራሪያዎች አይንበረከኩም፣እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ እንታገላለን!”ብሏል።
▶️የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በስልክ ተወያይተዋል።
▶️ሃማስ በጋዛ ውስጥ 8 ሩሲያውያን-እስራኤላውያን እስረኞችን ለማግኘት እየሞከረ ሲሆን ላቭሮቭ “ለአስር አመታት የሚቀጥል አደጋ” እንዳለ አስጠንቅቋል።
▶️የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር በጋዛ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ማስፋፋት ያለውን አደጋ እና አፋጣኝ የእርቅ ስምምነት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተወያይተዋል።
▶️የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ወረራ በጋዛ ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እና የአለም አቀፍ ህጎችን መጣስ ጥልቅ ስጋት እንዳለን እንገልፃለን ብሏል።
▶️የኳታር ኤሚር እና የኢራን ፕሬዝዳንት በፍልስጤም ስላሉ ለውጦች ተወያይተዋል!
የኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወራሪው ሀይል በጋዛ ሊፈጽመው ያሰበውን የመሬት ወታደራዊ ዘመቻ ውጤቱ የከፋ እንደሚሆንና ከአካባቢው አልፎ በአለም ላይ ከባድ አደጋዎችን እንደሚያስከትል በድጋሜ አስጠንቅቋል።
▶️የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንድደረግና አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ለማምጣት ኮሪደሮች እንዲከፈቱ እንጠይቃለን ያለ ሲሆን አያይዞም እስራኤል በጋዛ ያደረገችውን የመሬት ኦፕሬሽን እናወግዛለን በማለት አክሏል።
▶️የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ወረራ ለማድረግ በያዘው አቋም ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት እና አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ የሚያስከትል አደገኛ ሙከራ መሆኑን እንገልፃለን ብሏል።
▶️የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሆስፒታል፣እንዴ UNRWAአይነት የእርዳታ ማእከል ወይንም ትምህርት ቤት ለሽብር ተግባር የሚያገለግል ማንኛውንም ኢላማ አንተወውም በማለት ከዚህ በፊት በአንድ ግዜ ከ500 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የሆስፒታል ጥቃት በግዜው ያስተባበለች ቢሆንም ዛሬ ግን እርሱን በማመን ለወደፊቱም በእብሪቷ እንደምትቀጥል ይፋ አድርጋለች!
▶️በዋሽንግተን እና በኒውዮርክ የተካሄዱ ሰልፎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በማውገዝ ጦርነቱ እንዲያበቃ ጠይቀዋል።
◀︎የቀድሞ የቱርክ የፍትህ እና ልማት ፓርቲ ዋና አማካሪ የጋዛ ጦርነት የእስራኤል እና የምዕራባውያን አጋሮቿን ጭካኔ የተሞላበት ገጽታ ይፋ አድርጓል በማለት አውግዟል።
◀︎ በለንደን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ፍልስጤምን በመደገፍ እና በጋዛ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲያቆም ጠይቀዋል።
▶️“እናስታውሳለን” በሚል መሪ ቃል “የአይሁድ ድምፅ ለሰላም” ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2023 በእስራኤል የቦምብ ጥቃት የተገደሉ 2,913 የፍልስጤም ልጆችን ስም አውጥቷል።ድርጅቱ በጋዛ ላይ ለደረሰው አስደንጋጭ ነገር ተጠያቂ ናት ሲልም ዩናይትድ ስቴትስን ከሷል።ምክንያቱም በእስራኤል ጦር እጅ ህጻናትን ከሚገድሉት ቦምቦች 80% የሚሆኑት አሜሪካ ሰራሽ ናቸው።እያንዳንዱ ህይወት ውድ እንደሆነ እና ይህን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም ሁሉም ሰው የተቻለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
▶️የእስራኤል ሚንስትር #ኤሎንመስክ በጋዛ ለሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት መወሰኑን አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል።
▶️የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ባለስልጣናት የጋዛን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ያሰበውን አረመኔያዊ ድርጊት ለማስቆም ለተኩስ አቁም ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሏል።
▶️ሮይተርስ ከዲፕሎማቶች አገኘሁት ባለው መረጃ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ሰኞ ይሰበሰባል።
▶️በጋዛ ሰርጥ የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ምስሎች የእስራኤል ወረራ በሆስፒታሉ አከባቢ ላይ ባደረሰው የቦምብ ጥቃት የደረሰውን ውድመት አሳይተዋል።
▶️የስፔን ሚንስትር ለአውሮፓውያን #ናታንያሁ የጦር ወንጀለኛ ነው.. በ #ጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስፔንን ተባባሪ እንዳታደርጉን ብሏል።
▶️የእስራኤል እስረኞች ቤተሰቦች ከ # ናታንያሁ ጋር ከተገናኙ በኋላ ዘመዶቻችን እንዲመለሱ የፍልስጤም እስረኞችን ከእስር ቤት እንዲወጡ እንደግፋለን በማለት የሀማስን አቋም ተጋርተዋል።
▶️ግብፅ የእስራኤል መሰናክሎች እርዳታ ወደ #ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ እንቅፋት ሆነዋል በማለት እንደለመደችው ከሳለች።ክስ ብቻ!
▶️የፍልስጤም የዜና አገልግሎት ከራማላ በስተሰሜን በምትገኘው በቢት ሪማ ከተማ ከወራሪው ሃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 6 ወጣቶች በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ቆስለዋል(ተገድለዋል?)
▶️የቤልጂየም ፓርላማ አባል የሆኑት ሲሞን ሞትኪን የ#አልጀዚራ ፎቶዎች ባይኖሩ ኖሮ በጋዛ የእስራኤል ዕለታዊ ወንጀሎች ወደ ምዕራቡ ዓለም አይደርሱም ነበር በማለት ለአልጀዚራ ያላቸውን አድናቆት የገለፁ ሲሆን እግረመንገዳቸውንም የምዕራቡ አለም ሚድያዎችን ተችተዋል።
▶️የፍልስጤም ቲቪ እንዳስታወቀው ኮሙኒኬሽን እና ኢንተርኔት ቀስ በቀስ ወደ ጋዛ ሰርጥ እየተመለሱ ነው ብሏል።
▶️አንድ ፈረንሳዊ #ጋዛን በሚደግፉ ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ከፈረንሳይ ፖሊስ ጋር ተጋጭቷል¡
▶️የፍልስጤም ቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች “ፓልቴል”እና “ጃዋል” የጥሪ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቀስ በቀስ በጋዛ ሰርጥ ወደ ሥራ እየተመለሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
▶️በጋዛ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጋዛ በስተደቡብ በሚገኘው በካን ዩኒስ በሚገኘው የ"ታሞስ" ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ላይ የወረራ አውሮፕላኖች ባደረሱት የቦምብ ጥቃት 10 ሰማዕታት እና ከ25 በላይ መቁሰላቸውን አስታውቋል።
https://ummalife.com/AbdelazizBinMuhammed
https://t.me/Seyfel_Islam