🕋ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ እና ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰሙ፡- "አንድን ሙእሚን ህመምም ሆነ ድካም፣ ጨንቀትም ኾነ ማስቸገር፣ ሀዘንም ሆነ ሀሳብ እንዲሁም በሽታም ሆነ እሾክ አይነካውም፡፡ አላህ በነሱ ሰበብ ኃጢአቱን የሰረዘለት ቢኾን እንጂ" (ቡኻሪይ 5641፣ ሙስሊም 6733፣ አሕመድ 8248)፡፡
🕋ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህ መልካም የሻለትን ባሪያውን በሙሲባህ (ኃጢአቱን ይሰርዝለት ዘንድ) ይፈትነዋል" (ቡኻሪይ 5645፣ አሕመድ 7436)፡፡
🕋"ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በጀነት) አብስር፡፡ እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡ እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች ችሮታም አልሉ፡፡ እነርሱም (ወደ እውነት) ተመሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡155-157)፡፡
🕋በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከእነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከእነዚያም ከአጋሩት ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው፡፡" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡186)፡፡
፣አሏህ ሆይ በመሃሪነትህ ማረን፣ ችሮታህንም እዝነትህንም አውርድልን፣ ፀጋህንም አታሳጣን... አሏህ ሆይ ካንተ ብቻ እንከጅላለን ክጃሎታችንን ሙላልን:: እገዛህንም እንሻለን እና እርዳን፣ ባንተ ላይ ሙሉ እምነታችንን አድርገናል እና በሌሎች ላይ የምንደገፍ አታድረገን አላህ ሆይ በጥበቃህ ጠብቀን በክብርህ አክብረን በጸጋህ አክብረን። በእዝነትህም ማረን አንተ ከአዛኞች ሁሉ በጣም አዛኝ ነህና