Translation is not possible.

ትላንት ለይስሙላም ቢሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ የሰብአዊ እርዳታ እንድገባ የተኩስ አቁም ስምምነት እንድደረግ የአረብ ሃገራት ድርጅት ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በ14 ተቃውሞእና በ45 ድምፀ ተአቅቦ በ120 ድጋፍ ማፅደቁ ይታወቃል…ከወሬ የዘለለ ምንም ማድረግ ባይችልም!

በዚህ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ድምፀ ተአቅቦ ካደረጉ ሃገራት መካከል #ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን በጣም አግራሞት የጫረው ግን የ #ዒራቅ እና #ቱኒዚያ ተወካዮች ድምፀ ተአቅቦ ማድረግ ነበር!

ሆኖም የሁለቱም ሃገራት ተወካዮች ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉበትን ምክናየት ያብራሩ ሲሆን፣ዋነኛ ምክናየታቸው ረቂቅ ሀሳቡ እስራኤል በግልፅ የማያወግዝ ከመሆኑም በተጨማሪ የፍልስጢን እና የእስራኤል ተጎጅዎችን በእኩል እይታ የሚያቀርብ በመሆኑ ይሄ ደግሞ ተወክለው የሄዱበትን ሃገር አቋም የሚፃረርና ሌሎች ሸፍጦች ያሉበት በመሆኑ ነው ብለዋል!

በነገራችን ላይ ዒራቅም ሆነች ቱኒዝያ ለእስራኤል ሃገርነት እውቅና አይሰጡም!!

በኢትዮጵያ የፍልስጢን አምባሳደር ወይንም የፌደራል መጅሊስም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ድምፀ ተአቅቦ ያደረገበትን ምክናየት ማብራሪያ ቢጠይቁና ብንሰማው ግን ደስ ይለኛል!

https://t.me/Seyfel_Islam

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group