Translation is not possible.

#እስራኤል፡ ሶስተኛውን የአለም ጦርነት ለመጫር የሔደችበት ርቀት

የእስራኤል የቀኝ ክንፍ አክራሪ ጽዮናዊያን ፖለቲከኞች አካሔድ 3ኛውን የአለም ጦርነት ቀስቅሶ «በደም-ፍሳሽ» ስሌት ለመጠቀም ያለመ ይመስላል።በሙስና እና በፖለቲካዊ ዋልጌነት መደቡ ተነቃንቆ የነበረው የናታንያሆ ካቢኔ በሩን ለሐማስ ብርግድ አርጎ ከከፈተ በሗላ የደረሰው ጥፋት እድፉን ሸፍኖለት ጭቅቅቱን በንጹሗን ደም ላይ እየታጠበ ይገኛል።

ጋዛን ለመቆጣጠር የተጀመረው ጦርነት ከሰማይ የሚወርድ መዓትን ቢያዘንብም በመሬት ላይ በሚደረግ ውጊያ የአስራኤል ጦር ለግዜው ድል የቀናው አይመስልም። ይህንንም ለመሸፈን ተተናኳሿ እስራኤል ግብጽ ላይ የሙከራ ጥቃትን እንድትፈጽም አድርጓቷል።የአሜሪካ የጦር መንደር ኢራቅ ውስጥ በድሮን ተመቷል የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል። የጦርነት አድማሱ ሰፍቶ ሶሪያ የአሜሪካንን ድብደባ ቀምሳለች።ከየመን ሚሳኤሎች ተወንጭፈው ኢላማቸውን ሳይመቱ መሐል ላይ መክነዋል።ኢራን የተነጣጠረባትን ኢላማ አውቃ የሚመጣውን ለመቀበል በተጠንቀቅ ላይ ናት።ብቸኛዋ ሙስሊም የኔቶ አባል የሆነቸው ቱርክዬ በውትድርናውም፣በዲፕሎማሲውም፣በፖቲካውም ሆነ በሚዲያ ዘርፍ የሚከናወነውን ፕሮፓጋንዳ ወጥራ ይዛለች።ሩሲያና ቻይና የሚገጥማቸውን እስትራቴጂክ ሲሣይ ለመጎናጸፍ ዘና ብለው እየጠበቁ ነው።

በአንጻሩ የምእራብ አገራት በዩክሬን ያላሳኩትን ጦርነትና የተከናነቡትን የሐፍረት ማቅ በመግለጽ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ላይ ገብቶ ለመፈትፈት አይናቸውን በጨው አጥበዋል።ያለ አሜሪካ እርዳታ «እፍ ሲሉት ጭልጥ» የሆነው የአስራኤል የወታደራዊ ሐይል አገራትን አባልቶ የሚያተርፈው ትርፍ በውል ባይታወቅም ቁማሩን መጫወቱን ቀጥሏል።

ከሐማስ ጋር በተደረገው ጦርነት እስራኤል ከሰማይ የተከለከለ ኬሚካልና ቦንብን በማርከፍከፍ ግንባታን እያፈረሰች ንጹሗንን በመግደል ያስቆጠረቸው ድል መኖሩ ባይታወቅም ታላቅ የህዝብ ግንኙነት ኪስራ እያንፈራፈራት ነው።የጽዮናውያኑ ንቅናቄ የተቆጣጠራቸው አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሗን የአለማችንን ህዝብ እሳቤ መቆጣጠር አልቻሉም።ባንኮችን የተቆጣጠረው የጽዮናውያን ስብስብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ረብጣ ዶላሮችን አርከፍክፎ የአስራኤልን የቀኝ ክንፍ አክራሪ ፖለቲከኞች ቅዠትን ለመሸጥ ቢጥርም የፍልስጤማውያን እውነት ገዝፎበታል።

የአስራኤል ፖለትቲከኞች ቅዠትና የጦርነት ቤተ ሙከራ የመላው አይሁዶች ጥቃት ለማስመሰል የሚደረገው ጥረት በመላው አለም ባሉ «ንቁ» አይሁዶች እየመከነ ነው።«በኛ ስም አትነግዱም!» የሚሉ አይሁዶች ለአመታት የለሆሳስ ሆኖ የቆየው ድምጻቸው አፈናውን አልፎ እያስተጋባ ነው።

አሜሪካ ፈልጋውም ይሁን ሳትፈልገው በናታንያሆና ግብረ አበሮቹ ወጥመድ ውስጥ እየተሳበች እየገባች ነው።በኢራቅና በአፍጋኒስታን ጦርነቶች የአሜሪካ ህዝብ የኪስራ ገፈት ቀማሽ ቢሆንም የ2024 ምርጫ ከመድረሱ በፊት በሙስሊሞችና በአረቦች ላይ ጦርነት በመክፈት «እየተጠቃን ነው» የሚል የአዞ እንባ ትርክትን ለመፍጠር የሚደረገው ሽርጉድ ቀጥሏል። ተወዳዳሪዎቹ ገና ካሁኑ ለአሜሪካ ህዝብ በሚሰሩት ሳይሆን ባንክንና ሚዲያን ለተቆጣጠሩት ጽዮናውያን እጅ በመንሳት «እኔ ከአስራኤል ጎን ነኝ» የሚለውን ምጸት ማስማታቸውን ጀምረዋል።

ባንጻሩ በሙስሊምና በአረብ አገራት ያሉ መሪዎች የህዝባቸውን ግፊት እየቻሉት አይደለም። መንግስታቱ የእስራኤልን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በዲፕሎማሲ፣በገንዘብና በውትድርና ካልተባበሩ ወንበራቸው ይናጋል።አረብ አገራት ከእስራኤል ጋር የጀመሩትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የማስረጽ ሒደትን ሐማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን መስዋእት እንዲሆኑ አድርጎ ለአመታት እንዲሰናከል አድርጎታል ቢባል የእብለት አይሆንም።

በዚህ ቀውስ አሸናፊ ሆኖ የሚውረገረግ ሐይል አይኖርም።ገዳይም አስገዳይም ተሸናፊዎች ናቸው።ግን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ትርፋቸውን በሰዎች እልቂት ያደረጉት ሐይሎች ምን ያህል ሰው ቢያያልቅ ነው የሚረኩት የሚለው ጥያቄ በቀጣዮቹ ሳምንታትና ወራቶች ውስጥ ብቻ የሚፈታ መሆኑ አሳሳቢ ነው።

በድሜ የገፉ የእስራኤል ፖለቲከኞች በ1967 እ.ኤ.አ በአሜሪካ እርዳታ በስድስት ቀን ጦርነት የአረብ ይዞታዎችን ነጣጥቀን ድልን አድገናል በሚሉት የመንጠራራት፣የጉራና የማን አለብኝነት እሳቤ እንደተወጠሩ ነው። የአለም ቅኝ ገዢ እስኪመስሉ ድረስ ለአለም አቀፍ ህጎች ታዛዥ አለመሆናቸውን እያሳዩ ነው።አሁን 1967 አይደለም። የአላማችን ህዝብ ብዙ ነቅቷል።የአሜሪካም ህዝብ በምከፍለው የቀረጥ ገንዘብ ለምን ንጹሗን ያልቃሉ? የአንዲትን ትንሽ አገር ጦስ በምን እዳችን ነው የምንሸከመው? የሚል ጥያቄ እያስተጋባ ነው። ጦርነቱ በመሬትና በሰማይ ብቻ ሳይሆን ወደ ሳይበርም አለም አድጓል።አዲሱ ትውልድ ደግሞ የሳይበሩን ብቃት ተክኖበታል።የአስራኤል ሶስተኛውን የአለም ጦርነት የመጫር ተግባር የት ያደርሳታል? ግዜ ምላሽ ይሰጠናል።

አላህ ሰላማዊ ህዝቦችን ከሴረኞች ሴራ ይታደግ።

ልብ ያለው ልብ ይበል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group