Translation is not possible.

“ከደግነትም በላይ ምርቃት፥ ከክፋትም በላይ እርግማን የለም”!

የሼህ ሰይድ-ጫሌ መስጅድ ከተጀመረ እነሆ! ዓመታት ተቆጠሩ። ሚሊዮናት ወጭ የሚጠይቀውን ስራ፣ ሼህ ሙሐመድ-ነጅም በኢኽላስ ብቻ ጀመሩ። እሩቅ ነው ነገሩ። አሁን የመስጅዱ ግንባታ እየተገባደደ ነው። ጥቂት ግለሰቦች ያለ-እርህራሄ የተሳተፉበት፣ ታሪካዊ፣ ሀገራዊ እና አኺራዊ አሻራ ነው። ከህሊና በላይ የዋለ አንድ ግለሰብ፣ በእኔ በኩል ተመስጋኝ ነው(ዛሬም ከጭንቅ ስለገላገለን)።

አቶ ጀውሀር ሐሰን፦ ከዚህ ቀደም የመስጅዱን ሙሉ የብረት አቅርቦት ብቻቸውን ሸፍነዋል። ከ400,000 ብር በላይ አውጥተዋል። የመስጅዱን የጣራ ቆሮቆሮ+ጎረንዳ+ሚስማር+ማገር ብቻቸውን ሸፍነዋል። ከ800,000 ብር በላይ ፈጅተዋል። ይህንን ሁሉ ለማድረግ ብዙ ደጅ አላስጠኑም። ግርግር አልጠየቁም።

በተራ መልዕክት(Message) ብቻ አድራጎታቸውን ከውነዋል። ከመስጠታቸው ይልቅ አሰጣጣቸው ልብ ይወስዳል። ሼህ ሙሐመድ-ነጅምን'ንኳን አግኝተው፣ አውርተውም አያውቁም። የማስወራትና የማውራት ፍላጎትም የላቸውም። ለመታዎቅና ለመታየት አይሹም(እኛም ለአርዕያነት ነው ገለጻችን)። የሆነ ነገር ያደረጉ ያኽልም ስሜት አያንፀባርቁም። አድርገው፣ ዝም! ይኽን ዓይነቱን ቸርነት ምን ይሉታል? እንዲኽ መለገሥስ ምን ይባላል?

ሼህ ሰይድ-ጫሌ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲገጥማቸውም ይመስላል፦ ‹‹ከደግነትም በላይ ምርቃት፥ ከክፋትም በላይ እርግማን የለም›› ይሉ እንደነበረ ይነገራል። ‹ጥሩ መስራት እራሱ ምርቃት ነው› ማለታቸው ይመስላል። ለቅዱሳን እና ለደጋጎች ጥሩ ለመዋል ደግሞ በጣም መመረጥም ያሻል። በበኩላችን ቸሩን የመመረቅ ሞራል ያንሰናል። ዱዓ ግን አድርገናል። ዛሬም ነገም እናመሰግናለን፣ ለታሪክ የሚቀመጥ እሴትም ይኾናል።

የመስጅዳችን የጣራ-ማልበስ ሂደት ከሰሞኑ ይጀመራል። የከተማ ባለ-ሀብቶች ቀደምት የዕውቀት ማዕከላትን ጠግኖ የማደስ እና አቆይቶ ለትውልድ የማሸጋገር ትኩረት ቢኖራቸው፣ ዘርፈ ብዙ ስኬት ይኾናል። እኛ ከዚያም በላይ የቱሪዝም አካልና የሀገር ሀብት የማድረግ ሰፊ ፕሮጀክት ሰንደናል። አላህ ይገዘን!!

(ምስል፦ በ11/02/15 የተወሰደ የሼህ ሰይድ-ጫሌ የመስጅድ ግንባታ ሂደት)

Kedir Taju

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group