Тарҷума мумкин нест.

⚡️:::::::::ሕይወት::::::::::⚡️

ህይወትን ስረግም በደሏን ስቆጥር፡

ማማረሬ በዝቶ ስቃዬን ሳበጥር፡

ሁሌ ጠዋት ማታ ስተኛም ስነሳ፡

ፊቴ እንደጠቆረ ውስጤም እንደሳሳ፡

ባለማስተዋሌ ቀኙ ቢሆን ግራ!

መውደቅ መነሳቴ በሰዎች ቢወራ፡

ራሴው ከራሴው ስሟገት ከርሜ፡

ጭንቄ ሲበረታ ሲጠና ህመሜ፡

ከትዝታ መረብ መውጫ መንገድ ሳጣ፡

አንዱን ተወጣሁ ስል ሌላኛው ሲመጣ.፡

ለጊዜውም ቢሆን ህይወት ብርቱ ሰልፍ ሆና፡

ልጨብጣት ስጥር ብትመስልም ደመና፡

ሁሉን ስጋፈጠው በእምነት!ውስጥ ሆኜ፡

ሁሉን ቻዩን አምላክ ጌታዬን አምኜ፡

ምን ቢበረታ እንኳን የምድር ፈተና፡

ለማለፍ ችያለሁ በአንድዬ ስፅናና!

የኃላ ኃላ ግን ሲገባኝ ሚስጥሩ፡

መኖሬን ወደድኩት

ለካስ...

ሀዘን እና ጭንቀት ሀሴቴን የማግኛ ድልድዮች ነበሩ፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group