"የባከነው የአፋር ድንግል መሬቶች ልክ እንደ አባይ ለእናት ሃገራችን ሊበጁ ጉዞዉ ጀምረዋል"‼️
=========================================
አፋር ሰፊና ለጥ ያለ መሬት ለምርት የሚሆን አፈር ታቅፋ ለዘመናት ምንም ሳይመረትበት ልክ እንደአባይ ሲባክን ቆየ። አዋሽን የመሰለ ወንዝ ታቅፈው መስኖም ሆነ የመኸር ምርት ሳያሳዩን በበረሃነት ተሰይሞ የቆየው ምድር ዛሬ ቀን ወጣለት! ይሄ ትውልድ ግን ምነኛ እድለኛ ነው። አባይን ወደቤቱ መለሰ እንገና የአፋርን ጋሻ መሬት ለአለም ሊያመርትበት ነው። በነገራችን ላይ የአፋር መሬት እንኳን ኢትዮጵያን አፍሪካንና አለምን የመመገብ አቅም ያለው ሰፊ መሬት ነው። ከዚህ ውጪ ልዩ የሚያደርገውና በምርቱ ተዓምር ያሳያል የተባለው ሳይታረስ የኖረ መሆኑ ነው። አፋር መሬቱ ጠቅላላ ድንግል ነው። አሁን በጠቅላይ ሚኒስትር ፈር ቀዳጅነት መላው የአፋር መሬት ስንዴ ሊያመርት ዝግጅቱን ጨርሷል። አዋሽም ያለጥቅም የአፈር ሲሳይ ብቻ መሆኑ አብቅቶ ስንዴ ሊመግበን በአፋር ሜዳ ላይ ሲሽሎክሎክ ሊውል ነው። አፋር ሲጠራ ከዚህ በኋላ ጨውና ግመል ብቻ አይታወስም። ሉሲ ብቻ አትታወስም። ስመ ገናናዋና የሉሲዋ ሃገር አፋር እውቅናዋ በስንዴም በአለም መድረክ የሚመዘገብበት ቀን ቅርብ ነው።