Translation is not possible.

ከዚህ ዘመን ስልጣኔ የድሮ ጃሂሊያ በስንት ጣዕሙ! 

ሂሻም ኢብኑ ዐምር ሙሽሪክ ሰው ነበር።ረሱል ሰዐወ ከጎሳዎቻቸው በኑ ሀሺምና በኑል ሙጠሊብ ጋር ማእቀብ ተጥሎባቸው የነበረበት ወቅት ነው።

አምባገነኗ ቁረይሽ ለበኑ ሀሽሞች ላይሸጥ ላይለወጥ ላይዳር ስምምነት ፈርማ ካዕባህ ላይ ሰቅላ ነበር።ይህም ማዕቀብ ሊነሳ የሚችለው ረሱልን አሳልፈው ከሰጡ ብቻ  እንደሆነ ተስማምተዋል።

መካ ያኔ የምታራምደው የብሄር ፖለቲካ ስሪቱ ይህ  ስለነበር ሙሽሪክ የበኑ ሀሺምና በኑል ሙጠሊብ ጎሳዎችም ሰለባ ተደረጉ።ማእቀቡን ሁሉም ቁረይሽ ባይስማማበትም  3 አመት ሙሉ ምግብ ሳይጠፋ እየተራቡ ገንዘብ ሳይጠፋ የሚሸጥ እየጠፋ ፍዳቸውን አዩ።

ሰሃቦች ይህንን መሪር ጊዜ ተሰቃዩ የሞተው ሞተ። በህይወት ያለውም ቅጠል በላ። ከፊሉ የበሰበሰ ቆዳ ከመንገድ ላይ እያነሳ ጠብሶ የበላም ነበር። ረዲየላሁ ዐንሁም።

በዚሁ መሃል ሂሻም ዝምድናና የደም ትስስር ይዞት በድብቅ የአቅሙን ለሊት ላይ ምግብ ያደርስ ነበር። ጉዳዩ ውስጡን ስለከነከነው  ይቀርበኛል ወዳለው ሌላ ሰው ዘንድ ሄዶ–  «ዙሀይር ሆይ!  የአክስቶችህ ልጆች ማዕቀብ ውስጥ የሚቀምሱት አጥተው አንተ ምግብና ውሃ ይወሰድሃል?» አለው ።

ዙሀይርም ፦ «ወየውልህ! እኔ አንድ ሰው ነኝ ምን አደርጋለሁ ብለህ ነው?  ወላሂ አንድ የሚያግዘኝ ሰው ባገኝ ወረቀቷን ሄጄ እቀዳት ነበር»  አለው። ሂሻምም እኔ አለሁ አለው።ሶስተኛ ሰው ፈለጉ እሱም ውስጥ ያለ ተመሳሳይ ስሜት ነበር። በዚሁ አካሄድ አምስት ሰው ሞሉ።

ካዕባ ዘንድ በመሄድም ወከባ ፈጠሩ። ይህ ወረቀት ካልተቀደደ አንቀመጥም በማለት ረብሻ አስነሱ። ጉዳዩ ወደ ብሄር ግአጭት መሄዱ ስለተሰጋ የማእቀቧ ወረቀት ተቀደደች! ረሱልና በኑ ሀሺሞች ነፃ ወጡ! 

ልብ በል እነዚህን ሰዎች ያነሳሳቸው የደም ትስስር እንጅ ሙስሊም ሆነው አይደለም!

ዛሬ ላይ ጋዛ ዒራቅ ሶሪያ ሊቢያ በምእራባውያን ሲወድሙና ፍዳቸውን ሲያዩ እስልምናን የሚሞግቱ ውሳኔ ሰጪ መሪዎች አንድም አልቆጫቸውም ።

በርግጥ ስለ ኢስላምና ሙስሊሞች እንደማይሰሩ የሚታወቅ ነው። ግን ዐረብ ሆነው በደም መገናኘታቸው እንኳን ዙልምና ግፍን ለማውገዝ አላነሳሳቸውም! 

በጃሂሊያ ጊዜ የነበረው ሂሻም በግሉ ተነሳሽነት የ3 አመት ግፍን ማስቆም የቻለ ሆኖ ሳለ ተምረናል ሰልጥነናል የሚሉት የዐረብ መሪዎች በራሳቸው ጎረቤት ላይ የሚፈፀምን በደል ከማስቆም አንፃር የሂሻምን ያህል ካልተጓዙ በርግጥም ከነርሱ ስልጣኔ የድሮው ጃሂሊያ በስንት ጣዕሙ

Send as a message
Share on my page
Share in the group