7 month Translate
Translation is not possible.

ጀነት

ስምሽ የሚማርክ አንቺ ምርጥ ቦታ

የሙእሚን መኖሪያ  የጌታ ስጦታ

ገና አይኔም አላየሽ ሽታሽም አልመጣም

ልቤ ግን ተመኘሽ  አንቺን ለማጣጣም!

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

በፈተና አለም በሸር ተክብቤ

ሰይጣን ጓድ ሁኖኝ ሳይርቅ ካጠገቤ

በዱንዊ ፍቅር ተንበርክካ ልቤ

ወንጀል ተሸክሜ ሳይደክመው ወገቤ

ሱናን እረስቸ ወንጀል ተዘፍቄ

መቶበት አቅቶኝ ከአላህ እርቄ

ደግሞ አለማፈሬ አንችን መናፈቄ!!

*

ዋ!ምኞት...

የቀበርን ፈተና መኖሩን ዘንግቼ

አላህ ፊት መቆሙን ሂሳብ ረስቼ

የሲራጥን ድልድይ

የመህሸርን ፀሐይ

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

ይሄን ሁሉ ጣጣ ማሰቤንም ትቼ

ማንም ላያግዘኝ ላይቀርበኝ ወዳጄ

ስራየን ልቀብል መፅሀፌን በእጄ

ይህን ሁሉ ፈተና መኖሩን እያወቅኩ

ጀነት እመኛለሁ ወንጀል ላይ እንደቆምኩ!

منقول

Send as a message
Share on my page
Share in the group