Translation is not possible.

አንድ ግዜ በርካታ የተለያዩ ዐረብ ነገዶች እና አይሁዳውያን ተባብረው ረሱልን

ሰዐወ ከነ ተከታዮቻቸው ሊያጠፏቸው የመዲናን ከተማ ወረራ ለማድረግ ቀጠሮ

ያዙ።

ጠላት ወደ መዲና እንዳይገባ ነቢ ሰዐወ እና ሰሃባዎች ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው

ዳር ድንበሩን ይጠባበቁ ጀመር።

ጠላት ተጠራርቶ ሜዳ ሸንተረሩን ሞልቶ የመዲና አፋፍ ላይ ተከማቸ። ሰሀባዎች

እና ሙሽሪኮች ከጉድጓዱ ማዶ ለማዶ ይተያዩ ጀመር።

ከሙሽሪኮች ጎራ አንድ ዐምር የተባለ እጅግ ጨካኝ እና የሱ ጭካኔ ለምድር

ሰው ሁሉ ቢከፋፈል አለምን በጭካኔ ሊሞላ እምችል ግለሰብ ነበር።

ስለሱ ጭካኔ የማያውቅ እና እሱን የማይፈራ የአረብ ጎሳ አልነበረምም።

ሙሽሪኮቹ እና ሰሀባዎቹ ከጉድጓዶ ማዶ ለማዶ ሲተያዩ ድንገት ይህ ዐምር

የተባለ አውሬ ፈረሱን ጋልቦ ጉድጓዱን በመዝለል ከሰሀባዎቹ ዘንድ ተከሰተ።

«አንተ ሙሀመድ! ከኛ የሞተ የጀነት ነው ከሙሽሪኮች የሞተ የእሳት ነው ስትል

አልነበር? እኔ እሳትን ናፍቅያለሁ፤ ካንተ ሰዎች ጀነትን የናፈቀ ጀግና ካለ

ይሞክረኛ» ሲል ደነፋ።

የ25 አመቱ ዐሊይ ከረመላሁ ወጅሀህ ግብዣውን ተቀብሎ ለመውጣት

ሲነሳ፦«ዐሊይ! ይሄ እኮ ዐምር ነው፤ አላየኸውም እንዴ!» አሉት ረሱል ሰዐወ

ወጣቱ እንዳይቀጭባቸው ሰግተው።

«በአላህ ይዤዎታለሁ ዛሬ ጀነትን እንዳያስመልጡኝ» አላቸው፤ መጓጓት እና

ጀግንነት ፊቱ ላይ እየተነበበ።

ረሱል በጭንቅላታቸው ጠቅልለውት የነበረውን ዒማማ እና ሰይፋቸውን

ከማንገቻው አውልቀው ሰጡት።

ዐምር ሜዳው ላይ ከፈረሱ ጀርባ ሁኖ ከሙሀመድ ወገን እሚጋጠመውን ጀግና

በመጠባበቅ ላይ ሳለ ድንገት ለግላጋ ወጣት ሰይፍ ይዞ ከፊቱ ሲቆም፦ «አቤት

ማን ልበል?» በማለት ጠየቀው።

«እኔ የረሱል የአጎት ልጅ ነኝ» በማለት ዐሊይ መለሰለት።

«ወይ ዐሊይ! ልጅ ነህ ብለው ለሰይፌ ቀለብ እንዳደርግህ ነው እንዴ የላኩህ?»

ብሎ አፌዘበት።

«እኔ ተራ ስለሆንኩ ነው ወዳንተ የላኩኝ፤ ታድያ አንተ ማን ስለሆንክ ነው ደህና

ሰው እንዲወጣልህ ምትጠብቀው?» ብሎ ሞራሉን ከሰከሰለት።

«አንተ ልጅ እኔ እንደው አንተን ገድዬ አባትህን ማስደንገጥ አልፈልግም» አለው

ዐምር። አዛኝ ለመምሰል እየሞከረ

«እኔ ግን አንተን ገድዬ አባትህን ማስደንገጥ እፈልጋለሁ፤ ግና ከማፋለማችን

በፊት 3 ጥያቄዎችን አቀርብልኻለሁ» አለው ዐሊይ።

ዐምርም፦ «የመጀመርያው ምንድነው?» ብሎ ጠየቀው!

«በአላህ አንድነት እና በሙሀመድ መልዕክተኝነት እንድታምን ጥሪ

አቀርብልኻለሁ»

ይህን የሰማው ዐምርም፦ «ወላሂ ጭንቅላቴ ከእሳት ፍም ስር ቢገባ እንኳ ይችን

ቃል አልላትም፤ ባይሆን ሁለተኛው ምንድነው ንገረኝ» አለው።

ዐሊይም፦ «ረሱልን እንዳትዋጋቸው ወደ መጣህበትም እንድትመለስ

እመክርኻለሁ »

ንቀት በተሞላ አስተያየት እየተመለከተው፦ «ይህ ብላቴና ልኩን ሰርቶ አባበለው

እንዲባል ስለማልፈልግ አልመለስም» አለ።

«ሶስተኛውስ ምትለኝ ምንድነው?» ዳግም ጠየቀው።

ዐሊይም በኢማን ኩራት ወኔው ፈክቶ፦ «ሶስተኛው ምን መሰለህ! እኔ በእግሬ

ቆሜ እፋለምኻለሁ አንተ በፈረስህ ሁነህ እንደፈለግክ ተፋለመኝ።»

ዐምር ከፊቱ የሚያየው ለጋ ጎረምሳ ይህን ያህል ሲያፌዝበት ቁጣው ገንፍሎ

ሰይፉን ይዞ ተንደረደረበት።

ከጥቂት ፍልሚያ በኋላም ያ የዐረብያን ምድር ሲያስደነብር የከረመው ጀግናው

ዐምር በዐሊይ ሰይፍ አንገቱን ተቀንጥሶ ከሜዳው ላይ ተዘረረ።

የነብይህ ደረሳዎች ጀግንነት፣ ብልሀት፣ ዕውቀት፣ ኢማን ቀለቦቻቸው ነበሩ።

አክረመላሁ ዉጁሀሁም፤ ወሰላ ዐላ ነቢዪሂም....

_

ምንጭ፦

ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group