1 years Translate
Translation is not possible.

ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት አንድ ቢሊየነር ከቤት ውጭ አንድ ድሃ ሽማግሌ አገኘ። ‹በዚ ቅዝቃዜ ውጪ ላይ ኮት እንኳን አለበስክም አይበርድህም እንዴ› ብሎ ጠየቀው። አዛውንቱም "ኮት የለኝም ነገር ግን ለምጄዋለሁ ሲል መለሰለት። ቢሊየነሩም "ቆይ ጠብቀኝ ወደ ቤቴ ሄጄ ኮት አመጣልሀለው" ብሎት ሄደ።

ድሃው ሰውም በጣም ተደስቶ እጠብቅሀለው አለው። ቢሊየነሩ ወደ ቤቱ ደረሰ ግን በስራ ተጠምዶ ስለ ምስኪኑ ሰው ረሳ። በማግስቱ ጠዋት ድነገት ምስኪኑን አዛውንት አስታወሰና ሊፈልገው ወጣ ነገር ግን ምስኪኑን አዛውንት በቅዝቃዜው ሞቶ አገኘው።

ምስኪኑ አዛውንትም እንዲህ የሚል ደብዳቤ አስቀምጦለት ነበር "ሞቅ ያለ ልብስ ሳላገኝ ቅዝቃዜውን ለመቋቋም የሚያስችል የአእምሮ ጥንካሬ ነበረኝ, ነገር ግን እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባ, ቃልህ የአእምሮ ኃይሌን ገደለው"

ቃል መፈጸም ካልቻልን ምንም ቃል አንግባ። ለእርስዎ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል, ነገር ግን ለሌላ ሰው ሁሉም ነገር ሊሆን ይችላል!!!

ከማራኪ ወግ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group