Translation is not possible.

ቤተሰቡ በእስራኤል አየር ጥቃት የተገደሉበት የአልጀዚራው ጋዜጠኛ

------------------------------------------------------------------------------

የጋዛ ሰፈሮችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት የቀየሩት የእስራኤል አየር ጥቃቶችን በድፍረት ሲዘግቡ ከነበሩት አንዱ ዋኤል አልዳህዱ ነው።

ዓለም ትኩረቱን ሁሉ በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረገበት ወቅት አልዳህዱ ከጋዛ ተሰሚ ድምጾች አንዱ ሆኗል።

በባለፉት ሦስት ሳምንታትም የአልጀዚራ ተመልካቾች የማያባሩ የአየር ጥቃቶችን ከአልዳህዱ ዘገባ ሲከታተል ነበር።

ከጥቂት ቀናት በፊትም እንደተለመደው በማዕከላዊ ጋዛ የተፈጸመውን የአየር ጥቃት ሪፖርት አድርጎ ነበር።

በዚህ ጥቃት ግን ቤተሰቦቹ እንደተገደሉ አላወቀም።

ኑሴይራት በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ላይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት የሰባት ዓመት ታዳጊ ሴት ልጁን ጨምሮ ባለቤቱ፣ ሌላኛው ወንድ ልጁ እንዲሁም የልጅ ልጁ ተገድለዋል።

አልዳህዱ በዴይር ኤል ባላህ በሚገኘው የአልአቅሳ ሰማዕታት ሆስፒታል በአስከሬን ክፍል ውስጥ ከወንድ ልጁ አስከሬን አጠገብ ተንበርክኮ ሲያነባ፣ ፊቱን ሲነካካ እንዲሁም ባለቤቱ አስከሬን አጠገብ ተጎንብሶም አልጀዚራ አሳይቷል።

የሰባት ዓመት ሴት ልጁን ሻም ሕይወት አልባ አካል አቅፎ በደም የተለወሰ ፊቷን አተኩሮ እያየ ሲያነባም በርካታ ሚዲያዎች ተቀባብለውታል።ያረቡ ከንተው ፈርጁን ለወንዶሞቻችን አምጣላቸው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group