Translation is not possible.

አሜሪካ በሶሪያ ያሉ ወታደሮቿን ባጠቁ አካላት ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸማን ገለጸች

October 27, 2023

በሶሪያ እና ኢራቅ ባሉ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል

አሜሪካ በሶሪያ ያሉ ወታደሮቿን ባጠቁ አካላት ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸማን ገለጸች።

ከ20 ቀናት በፊት ለፍስልጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡

ይዚህ ጦርነት አሁንም መቀጠሉን ተከትሎ የዓለም ሀገራት ለእስራኤል እና ፍልስጤም የቀጥታ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ላይ ናቸው።

አሜሪካ ለእስራኤል የቀጥታ ድጋፍ ካደረጉ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ኢራን እና ሌሎች ሀገራት እና ቡድኖች ጎራ ለይተው ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው።

የየመን አማጺያንን ጨምሮ በሶሪያ እና ኢራቅ ያሉ ቡድኖች አሜሪካ በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ጣልቃ እንዳትገባም ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

ይሁንና አሜሪካ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ በቀጥታ ድጋፍ ማድረጓን ተከትሎ በሶሪያ እና ኢራቅ ባለው ወታደራዊ የጦር መንደሮቿ ላይ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል።

ዋሽንግተን በሁለቱ ሀገራት በደረሰባት የድሮን ጥቃት የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃለች።

አሜሪካ እንዳለችው በሶሪያ እና ኢራቅ ባለው የጦር መንደሮች ላይ ጥቃት የፈጸሙት በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ናቸው።

አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን ያሰማራች ሲሆን 900 ተጨማሪ ወታደሮችን ደግሞ በቅርቡ ወደ አካባቢው እንደምትልክ አስታውቃለች።

የእስራኤል-ሐማስ ወይም ፍልስጤም ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ኢራን እና ቱርክ ጦርነቱ ካልቆመ ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊዛመት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group