ሩሲያ የሀማስን ልኡካን ቡድን መጋበዟ ተገቢ መሆኑን ገለጸች
October 27, 2023
ፔስኮ እንደገለጹት የሀማስ ልኡካን ቡድን አባላት በሩሲያ ቆይታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካዮች ጋር ተገናኝተዋል
ሩሲያ የሀማስን ልኡካን ቡድን መጋበዟ ተገቢ መሆኑን ገለጸች።
ሩሲያ የሀማስን የልኡካን ቡድን ወደ ሞስኮ ለመጋበዝ ያሳለፈችውን ውሳኔ ትክክል ነው ተከላክላለች።
ይህ የሩሲያ ውሳኔ እስራኤልን አስቆጥቷታል።
የእስራኤል ጦር የምድር ኃይል የጋዛ ሰርጥ ዘመቻን ከዛሬ ጀምሮ በስፋት እንደሚያከናውን ገለጸ
የሩሲያ ቤተ መንግስት ክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ "በእስራኤል- ፍልስጤም ግጭት ውስጥ ያሉ ሀሉንም አካላት ማነጋገር አስፈላጊ ነው ብላ ታምናለች" ብለዋል።
ፔስኮ እንደገለጹት የሀማስ ልኡካን ቡድን አባላት በሩሲያ ቆይታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካዮች ጋር ተገናኝተዋል።
የስራኤል እና ሀማስ ግጭት ከተቀሰቀሰ ከሶስት ሳምንት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢራን እና የሀማስ ተወካዮች በሞስኮ መገናኘታቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት አስታውቋል።
ነገርግን ሚኒስቴሩ የውይይቱ ይዘት ምን እንደሆነ አልገለጹም።
በድርጊቱ የተቆጣችው እስራኤል ሩሲያ ሞስኮን እየጎበኙ ያሉትን የሀማስ የልኡካን ቡድን አባላትን እንድታባርር ጠይቃ ነበር።
ሩሲያ ከሀማስ ጋር የቆየ ግንኙት ያላት በመሆኑ እንደ አሜሪካ እና አውሮፖ ሽብርተኛ ድርጅት ብላ አልፈረጀችውም።