Translation is not possible.

.

ከእስልምና የእውቀት ማዕድ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

👉 ልዩ ልዩ 1

📖 በኢስላም መሠረታዊ ክንውኖች 5 መስፈርቶች ተቀምጧል።

1- ፈርድ ( ግዴታ) ፦

ይህ ክንውን አንድ ሰው ፈርድ ወይም ግዴታ የሆነን ነገር መፈፀም ግዴታው ሲሆን ቢያከናውን ሚንዳ ያገኝበታል። ነገር ግን ባያከናውን ይቀጣበታል።

2 - ሙስተሐድ (የሚወደድ) ፦

በዚህ ክንውን ደግሞ አንድን የሆነ ነገር ቢያከናውን ይመነዳበታል፤ ባያከናውን አይቀጣም።

3 - ሙባሕ (በምርጫ የሚወሠድ) ፦

አንድን ነገር ቢያከናውንም ባያከናውንም አይመነዳምም አይቀጣምም።

4 - መክሩሕ (የሚጠላ) ፦

ባያከናውን ሚንዳ ያገኝበታል ነገር ግን ቢያከናውን አይቀጣም። ለምሳሌ፦ ፍቺ መፈፀም

5 - ሐራም (የተከለከለ) ፦

ባያከናውን ሚንዳ ያገኝበታል፤ ቢያከናውን ይቀጣበታል።

[[[[ ኮሜንት ላይ ለ5ቱም ምሳሌ እንስጥ ]]]

👉 ልዩ ልዩ 2

📖 ሐዲሰቱ አል-ኢፍክ ፦ ምንድ ነው?

- እናታችን አዒሻ(ረዐ) ላይ መናፍቃን ያስወሩት የቅጥፈት ወሬ ሐዲሰቱ አል-ኢፍክ ይባላል።

📝 አሠርም ምንድ ነው?

- የቀደምት ደጋግ የአላህ ሰዎችና ነብያት መልካም ፋናዎች፣ምሳሌዎች ፣ ትውፊቶች ፣ ታሪኮች ፣ ወጎችና የመሣሠሉትን የሚተላለፍበት መንገድ አሠርም ይባላል።

ይህ ርዕስ በአላህ(ሱወ) 99 የመልካም ስሞች ትርጉም በሰፊው ይቀጥላል። like, share, follow ያድርጉ። ለተጨማሪ የሐይማኖት ንፅፅሮችን ለማግኘት ደግሞ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ t.me//AkeelComparative

Send as a message
Share on my page
Share in the group