Translation is not possible.

ያሳዝናል‼

========

✍ ጋዛን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያገናኝ የነበረው ብቸኛው የጀዋል ካምፓኒ ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት ገመድ በጽዮ'ናዊያኑ ቦምብ መመታቱን ተከትሎ ጋዛዊያን ድምፃቸው ታፍኖ ያለ ማቋረጥ ከ3 ሰዓታት በላይ የቆዬ እጅግ ዘግናኝ የቦምብ ጥቃት እየዘነበባቸው ነው።

በተጨማሪም በባህርም፣ በአየርም፣ በምድርም እሳት እየዘነበባቸው ነው።

ጠብቃ ጠብቃ እስራኤል ከሰሞኑ የከፋውን ጭፍ'ጨፋ ዛሬ በጨለማ ጀምራለች።

ከ40 ሺህ በላይ ታማሚዎች የሚገኙበትን ዋነኛውን አልሺፋ ሆስፒታልንም አጋይታለች።

አንድም ፈለስጢናዊ በህይዎት ማየት አት'ፈልግም።

አምቡላንሶች እንኳ ወደ ሟቾችና ቁስለኞች ዘንድ በማምራት ማንሳት አልቻሉም።

እስራኤል ወን'ጀሏና የምትፈጽመው ዘግናኝ ጥቃት ተቀርፆ በሚዲያ እንዳይወጣባት ድምጿን አጥፍታ ወገኖቻችንን እየ'ጨረሰች ነው።

ልክ በዚህች ቅፅበት በጘ-ዝ'ዛ ታሪክ ይቀር የማይለው የጦር ወ'ንጀልና የዘር ማፅ'ዳት ጭፍ'ጨፋ እየተፈጸመ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁንም በዝምታ ላይ ነው።

ሐስቡነ-ል'ሏህ ወ ኒዕመል ወኪል!

በጣም ነው የሚያሳዝነው! አላሁልሙስተዓን!

ቢያንስ በመልካም ዱዓችን አንርሳቸው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group