Translation is not possible.

✍📩አይሆንሽም

===========

ሱሪ እየገተተ የሚቁለጨለጨው፡

ሱናውን ተቃርኖ ፂሙን የሚላጨው፡

በለሥላሣ ድምፁ የሚወሰውሥሽ፡

ሊያማልልሽ እንጂ አይደለም ሊያገባሽ፡

በሶሻል ሚድያ በቃልም በተግባር፡

በቴሌ ግፘሙ በኢሞ በቫይበር፡

የፖለቲካ ወግ አምጥቶ አራጋቢ፡

ይህ ሰው አይሆንሽም እና እንዳታገቢ፡

የነብዩን ሱና በቢድዐ የተካ፡

ሹብሀ የሚረጭ ሥሜቱን ሊያረካ፡

ሁሌ የሚጮኸው ሥለፖለቲካ፡

ሀያሉን ፈጣሪ አላህን ያመፀ፡

ሱናን እየተወ ቢድዐን የቀረፀ፡

እንድህ አይነቱ ሰው እንደት ይሆንሻል፡

የሱናዋን ወጣት እንደት ያገባሻል??

የቢድዐው ቅርጫት ለአንችኮ አይሆንሽም፡

ለሱናዋ ጀግና ለባለ ኒቃቧ አወ አይመጥንሽም፡

አይሆንሽም!!

አይመጥንሽም!!!

ገና መጀመሪያ ትዳር ሲጠይቅሽ፡

መንሀጂ አቂዳውን ማጣራት አለብሽ፡

     ገባሽ?

በሥልክ ደውሎ የሚወሰውሥሽ፡

ሊያማልልሽ እንጂ አይደለም ሊያገባሽ፡

እንደሚፈልግሽ ወሬውን ከሰማሽ፡

ሀረካ ሰከናው ሁኔታው ከገባሽ፡

በቶሎ አሥቀድመሽ አትወሥኝ በቅፅበት፡

ይሆናል አይሆንም በጥልቅ አሥቢበት፡

አሥተውይ እህቴ ዘለሽ እንዳትገቢ ፡

ጀግና ወጣት እንጂ ፈሪ እንዳታገቢ፡

የቢድዐ አቀንቃኝ ፈሪ ነው ቦቅቧቃ፡

መንገዱ የጠፋው ታጥቦ ወደ ጭቃ፡

አጋጣሚ ሆኖ ቆርጦ ቢቀርብሽም፡

እርግጠኛ ሁኝ ይህ ሰው አይሆንሽም፡

አትቅረቢው አያዋጣሽም፡

ተጠንቀቂው ባል አይሆንሽም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group