Translation is not possible.

በጁምዓ ቀን በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!!

ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል!

አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ?

እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ»

አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል።

አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል።

«ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ!

አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል።

ከዚያም «ያ ሙሐመድ! አሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል።

«ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ »

አላህ ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደመስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ።

ከወርቅና ከሉል በተሰራ ግንብ ውስጥ ይነዳሉ። ባማረ መዓዛ ይታወዳሉ። ውስጥ የነበሩት የጀነት ሰዎች የተበለጡ እስኪመስላቸው ድረስ እነዚህ ሰዎች ውብ ይሆናሉ። ከዚያም ወደ ጀናህ እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜና ለዘልዓለም ጀሀነም ትዘጋለች!!

በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ፦

« ﺭُّﺑَﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ

እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ (ሱረቱ አል-ሒጅር - 2)

አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group