1 year Translate
Translation is not possible.

የጁሙዓ እና የጀማዓ ሶላት ግዴታነት

ወደፊት በሚመጡት ማስረጃዎች መሰረት የጁመዓ ሶላትና የጀመዓ (የህብረት) ሶላት በወንዶች ላይ ግዴታ ነው፡፡

1. አላህ እንዲህ ብሏል፡- እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዕለተ ጁሙዓ ለስግደት ጥሪ (አዛን) በተደረገ ጊዜ ፣አላህን ለማስታወስ (የዕለቱን ኹጥባ(ንግግር) ለማዳመጥና ሶላት ለመስገድ)ተንቀሳቀሱ (ሂዱ)፡፡ መሸጥንም ተው፡፡የምታውቁ ከሆናችሁ ይህ ለናንተ መልካም ነው፡፡

(አል-ጁሙዓ፡ 9)

2. ነቢዩ ✵ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በቸልተኝነት ሦስት የጁሙዓ ሶላቶችን የተወን ሰውአላህ በልቡ ላይ ያትምበታል፡፡(አሕመድ የዘገቡት ሐዲስ)

3. ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-‹‹ሶላት እንዲትቆምና ከዚያም ምክንያት ሳይኖራቸው እቤታቸው የሚሰግዱ(መስጂድ መጥተው የማይሰግዱ) ሰዎችን ሄጄ ላቃጥልባቸው በእርግጥ አስቤያለሁ፡፡(በኻሪ የዘገቡት)

4. ነቢዩ እንዲህ ብለዋል :« አዛን ሰምቶ ለሶላት መስጊድ ያልመጣ ሰው ምክንያት ያለው ካልሆነ በስተቀር ባለበት የሚሰግደው ሶላቱ ዋጋ ቢስ ነው፡፡»(ለምሳሌ ፍርሃትና በሽታን ይመስል) (ኢብኑ ማጀህ)

5. አንድ አይነ ስውር ሰው ወደ ነቢዩ መጣና ወደ መስጂድ መርቶ የሚወስደኝ የለኝም ብሎ የአላህን መልዕክተኛ መቅረት እንዲፈቅዱለት ጠይቆ ፈቀዱለት፡፡ዓይነ ሥውሩ ሰው አስፈቅዶ ወደ መጣበት ዞሮ ሲሄድ ነቢዩ ጠሩትና ፡-"አዛኑን ትሰማለህ?" አሉት፡፡ አዎን እሰማለሁ አላቸው፡፡እንግዲያውስ ጥሪውን አክብረህ ተገኝ ብለውታል፡፡(ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ)

6. «ነገ ሙስሊም ሆኖ አላህ ዘንድ መቅረብ የሚወድ ሰው ጥሪ በተደረገበት ሁሉ እነዚህን አምስት ዕለታዊ የግዴታ ሶላቶች በትጋት ይስገድ፡፡ አላህ ለነቢያችሁ መሪ(ቅን) ጎዳናዎችን የደነገገላቸው ሲሆን ሶላቶቹ ከቅን ጎዳናዎቹ ዉስጥ ናቸው፡፡ ከመስጂድ ቀርቶ እቤቱ እንደሚሰግደው ሰው እቤታችሁ ከሰገዳችሁ የነቢያችሁን ፈለግ (ሱና) ትታችኋል ማለት ነው፡፡የነቢያችሁን ፈለግ መከተል ከተዋችሁ ደግሞ(ohwam)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group