Translation is not possible.
ሐባን ኢብኑ ሙንቂዝ [ረዐ] እንደዘገቡት:
 
«አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዱዓዬን ሲሶ(አንድ አራተኛ) ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?»
 
እርሳቸውም:‐ «ከፈለግክ አዎን!» አሉት።
 
«ሁለት ሶስተኛውን ላድርገው?» አላቸው።
 
«አዎን!» በማለት መለሱለት።
 
«ሁሉንም ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?» ጠየቀ።
 
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐ «እንደዚያ ከሆነ ያሳሰበህን የዱንያም ሆነ የአኺራን ነገር አላህ ይገላግልሀል።»
 
ሹዐቡል‐ኢማን ላይ በይሀቂይ ዘግበውታል።
Send as a message
Share on my page
Share in the group