Translation is not possible.

ምዕራባዊያን ለእስራኤል ድጋፍ ማድረጋቸውን ፕሬዝዳንቱ ተችተዋል

ሐማስ የነጻነት ታጋይ እንጂ ሽብርተኛ አለመሆኑን ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ገለጹ፡፡

ከ20 ቀናት በፊት ለፍስልጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡

እስካሁን የዓለም ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ የሆነው ይህ ጦርነት መቋጫ ያልተገኘለት ሲሆን በየዠዕለቱ ሰዎች እየተገደሉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሐማስ ለፍልስጤማዊያን እና መሬት የሚታገል የነጻነት ድርጅት እንጂ ሽብርተኛ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ የብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ሌሎችም ሀገራት መሪዎች እስራኤልን ደግፈውጉብኝት አድርገዋል።

የቱርክ ፕሬዝዳንት የእስራኤል ጉብኝታቸውን ሰረዙ

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን እስራኤልን የመጎብኘት እቅድ የነበራቸው ቢሆንም ጉብኝታቸውን ሰርዘዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጉብኝታቸውን የሰረዙት እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያደረሰችው ያለው ጥቃት በመቀጠሉ ምክንያት እንደሆነ አናዶሉ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ምዕራባዊያን እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያደረሰች ያለውን ጥቃት አለማውገዛቸውን ተችተዋል።

የሙስሊም ሀገራት በጋዛ ጉዳይ ትብብር እንዲያደርጉ የጠየቁት ፕሬዝዳንት ኤርዶሀን እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆምም አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው እስራኤል በጋዛ ጦሯን እንዳታሰማራ እና ለፍልስጤማዊያን ሰብዓዊ ድጋፍ እየተጓዘበት ያለው የራፋ ድንበር እንዳይዘጋ ብለዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group