✍ወንድማዊ ምክር
እንደማስመሰል ሰውን የሚጎዳ ነገር የለም።
ቀን ጨዋ መስሎ ለሊት ነውርኛ መሆን እጅግ እኩይ ና ክፉ ተግባርነው።
👉ክፉ አመል ክፉ በሽታ ነው።እንድህ አይነት አካሄድ ህይወታችንን ብቻ ሳይሆን አሟሟታችንም ያበላሽብናል እንጠንቀቅ።
⚠️ለሰው ብለህ አትኑር። ራስህን ሁንና ኑር።
አንተ ሁሌም የሰው ኮፒ ፔስት ሆነ መኖር ሀቂቀተን ሁለቴ መሞት ነው።
👉አንተ የአሏህ ብቻ እንጂ የማንም ባሪያ አይደለህም። አዕምሮህን ና ራስህን ጠብቅ።
ለየተኛው ህይወት ነው ከሰው እየተመሳሰልክ ና ሰውን እየተለማመጥክ የሚትኖረው???
መንሀጅህን የሚትቀያይረው???ሆየ ሆዬ ይመስል ከሁሉም የሚታጨበጭበው??????በየቻናሉ እየዞርክ ???የቲቪ ቻናል መሰለክ የነብዩዲን???
❌የእነ እከሌ ተከታይ ነኝ የሚትለው???
قال عبدالله بن مسعود رضي الله عنه
ዓብደህ ኢብኑ መስዑድ አላህ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና…
لا يكون أحدكم إمَّعَة
👌አንዳችሁ ከእከሌ ጋር ነኝ አይበል።》አሉ
✍قالوا : وما الإمَّعَةُ يا أبا عبد الرحمن ؟
👉ሰሃቦችም 《ከእከሌ ነኝ አትበሉ ማለት ምን ማለት ነው? በማለት ጠየቁና
✍قال : يقول: إنما أنا مع الناس إِن اهتدوا اهْتَدَيْتُ ، وإِن ضَلُّوا ضَلَلْتُ ..!
✍ዓብደላህ ኢብኑ መስዑድም እኔ የምከተለው የእምነት ጎዳና(ዓቂዳ ወይም ሚንሀጅ እነ እከሌ ሚከተሉትን ዓቂዳ(ሚንሀጅ) ነው አትበሉ።
ያ ሰው ከካደ(ከከፈረ) ልትክዱ(ልትከፍሩ) ነውን??
🍏ألا ليُوَطِّنُ أحدكم نفسه على إِنْ كَفَرَ الناس أَنْ لا يَكْفُرَ
👌አንድ ሰው እምነቱን(ኢማኑን) ሰዎች ሁሉ ቢክዱ(ቢከፍሩ) እንኳን እንደማይከፍር(በአላህ እንዳማይክድ ያህል አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻል አለበትና።
📚الطبراني في الكبير(٨٧٦٥)
✍የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ዲን ከያዝክ ቡሃላ ራስህን የማንም መጫውቻ ማድረግ የለብህም ። እውነትነው ፈተና በዝቶብህ መጠጊያ አጥተ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለሁሉም ነገር ሷብር እናድርግ።
👌 የዲን ፈተና ሀቂቃ ከባድ ነው ።
ነገር ግን የዲን ፊትናን የሚቋቋሙ እነማናቸው?
الفتنة يفتضح عندها خلق كثير ..
👌ፊትና አብዛኛዎቻችንን የሚሸውድ ክስተት መሆኑን ያውቃሉን??
✍قـال أبو بكر اﻵجــري رحمه
አቡበክር አልአጁሪይ አላህ ይዘንላቸውና
✍فإن الفتن على وجوه كثيــرة:
የፊትና ምንጮች ብዙ ሲሆኑ
✍قــــد مضى منها فتن عظيمة..
በቀደምቶቻችን(በሰለፎቻችን) ወቅት እጅግ ብዙና ታላላቅ የሚባሉ አደገኛ ፈተናዎች ተከስተው አልፈዋል
نجا منها أقوام ..
ይህንን ፈተና በፅናትና እጅ ባለመስጠት በትዕግስት ያመለጡ ሲኖሩ
👌وهلك فيها أقوام :
ትዕግስትና የአላማ ፅናት በማጣት በፈተናው ወድቀው የቀሩም ነበሩ
ለዚህም ውድቀታቸው ከዋና ዋና ምክንያቶች መካከል
✍باتباعهم الهوى!.
1ኛ:ዝንባሌያቸውን(ስሜታቸውን) በመከተላቸው እና
👌وإيثارهم للدنيا.
የዚህቺን አለም(የዱኒያን) ሂይወት ከአኼራ ምንዳ በማስበለጣቸው ነው።
👌 فمن أراد الله تعالى به خيرا
አላህ መልካምን(ውጤታማነትን) የፈለገለት ሰው
👌فتح له باب الدعاء.
🍏1ኛ_ዱዓ የማድረግ ፍላጎት በርን ይከፍትለታል
👌 والتجأ إلى مولاه الكريم.
🍎2ኛ_ወደ ፈጣሪው ወደ አላህ የመመለስንና የመጠጋትን በር ይከፍትለታል
👌 وخاف على دينه.
🍎3ኛ_በዲኑ መፈተንን መፍራትን(መጠንቀቅን)ይለግሰዋል
👌 وحفظ لسانه.
🍏4ኛ_ምላሱን መቆጣጠርን ይሰጠዋል
👌وعرف زمانه.
🍎5ኛ_ያለበትን ዘመን ተጨባጭ(እውነታ) መገንዘብን ይሰጠዋል
👌ولزم الحجة الواضحة؛ السواد الأعظم.
🍏6ኛ_ዲኑን በተመለከተ ቀጥተኛ የቁርአንና የሀዲስ ማስረጃዎችን አጥብቆ መያዝን ይሰጠዋል።
👌 ولم يتلون في دينه.
🍏7ኛ_ከሁሉም ጋር ከመመሳሰልና ሁሉም ጋር አለው ከማለት ይጠብቀዋል።
👌 وعبد ربه تعالى.
🍎8ኛ_አላሀን በማምለክ ላይ ብርታትን ይለግሰዋል።》
👌فترك الخوض في الفتنة.
🍏9ኛ_በፊትና ላይ ከመሳተፍ ይጠብቀዋል።
👉ምክንያቱም
✍فإن الفتنة يفتضح عندها خلق كثير».
👉ፊትና የአብዛኞ ድብቅ ማንነት የሚጋለፅበት ክስተት ነውና።》ብለዋል
📚المصدر :الـشـريعـة (١/٣٩٢)
✍ በሐቅ ላይ መፅናት እና ለሰዎች አሉባልታ ቦታ አለመስጠት።
لا تبال_بكلام_الناس
قال العلامة الشيخ محمد ابن عثيمين رحمه الله
✍ሸይክ ሙሀመድ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና
لو أن الإنسان سمع ما يقول الناس وما يعترضون به ما مشى خطوة ،
👌《አንድ ሰው ሰዎች የሚሉትንና ትክክለኛውን የኢስላም አስተምህሮት(ሱናን) ላለመተግበር የሚያቀርቡትን አማራጭ የሚያደምጥና በፀጋ የሚቀበል ከሆነ በሀቅ ላይ አንድ እርምጃን እንኳን መራመድ አይችልም።
👌 لكن أنت أصلح ما بينك وبين الله ولا يهمك أحد ، فالكلام على إرضاء الله عز وجل ،
👌ስለዚህ ማንኛውም ሰው ዋነኛ ውጥኑና ግቡ ሊሆን የሚገባው ከአላህ ጋር ያለውን ግንኙነት ማስተካከልና ማሳመር ብቻ ነው ።
ማንኛውም ሙስሊም ከአላህ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ላይ ትንሽ እንኳን ሰዎች ምን ይሉኝ የሚለው እሳቤ ሊኖረው አይገባም።
እንደ ኢስላማዊው አስተምህሮት ትልቁ ቁምነገር አላህ ጋር መወደድና መወደድ ብቻ ነውና።
فإذا التمست رضا الله بسخط الناس رضي الله عنك وأرضى عنك الناس وكفاك مؤونتهم .
📚المصدر:
(التعليق على الإقتضاء (١٧٠/1)
✍ አንድ ሰው እንደ ኢስላም አላህ የሚወደው ነገር ግን ደግሞ ሰዎች የማይወዱት ነገር ገጥሞት የአላህን ፍቅር ፈልጎ አላህ የሚወደውንና ሰዎች የማይወዱትን ነገር በመተግበር አላህ እንዲወደው ለማድረግ ሲል ሰዎችን ካስቀየመ አላህ ወዶት ሰዎችም እንዲወዱት ያደርገዋል።
ምንጭ📚አታዕሊቁ ዓልል ኡቅቲዳእ(1/170)
﴿وَإِن تُطِع أَكثَرَ مَن فِي الأَرضِ يُضِلّوكَ عَن سَبيلِ اللَّهِ إِن يَتَّبِعونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِن هُم إِلّا يَخرُصونَ﴾
📚سورة الانعام(116)
🍏ልቅናው የላቀው አላህ
ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ. ሆይ አብዛኛው ሰዎች የሚሉህን ካደመጥክ ከትክክለኛው የእምነት ጎዳና ያሳስቱሀል ምክንያቱም አብዛኛው ሰዎች መላምትን አራማጅ ውሸታም ናቸውና ብሎዋል።
📚ሱረቱል አንዓም(116)
✍በአሏህ ዲን ለጥቅም ብለን ከቦታው ጋር የሚሄድና ድምቀት ያለውን የተለያዩ ቀለምና ዲኮር እየተቀባን ከሁሉም መመሳሰል ይቅርብን።ከማስመሰልና ከመለዋወጥ አሏህ ሁላችንም ይጠብቀን።
አሏህ ሆይ ውጫችንንም ውስጣችንንም የበጀ አድርገው።