Translation is not possible.
➭, ለአድስ ሙሽሮች
💍💍
በጋብቻ ቀን ለሊት የሚፈፀሙ ተግባሮች
 
1፡- ባገባህበት ወቅት የምታደርገው ድንቅ ዱዓ..👇
 
“አላሁመ ኢኒ_አስአሉከ ኸይረሃ ወኸይረ ማ ጀበልተሃ ዓለይሂ ወአኡዙ ቢከ ሚን ሸሪሃ ወሸሪ ማ ጀበልተሃ አልይሂ
 
አላህ ሆይ! እኔ የዝችን ሴት መልካም ጎን እና እንድታዘነብል ያመላከትካትን በጎ ነገር እጠይቀሃለሁ፤ ከተንኮሏና ካዘነበለችበት መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ)፡፡”
 
2፡- የሰርግህን ቀን ዉሎ ካሳለፍክ በኋላ ምሽት ላይ ሚስትህ ጋር አንድ ላይ ስትሆኑ ብቸኝነት ይሰማታል፣ ፍርሀት ይወራታል፣ሀፍረት ይሰማታልና አጫውታት፣ ዘና አድርጋት!
 
3፡- ረከዓተይን አሰግዳት፡፡ ይህ ሶላት ባል የቤቱ አባወራና አስተዳዳሪ እንዲሁም ጠባቂ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ሁለታችሁም በዛ ለሊት ፍርሃት እንዳይሰማችሁና ለወደፊት የትዳር ህይወታችሁ መሳካት ጥሩ አስተዋፅኡ አለው፡፡
 
4፡- ወተት አጠጣት (ይህ ለርሷ መረጋጋትን ያደርግላታል)፡፡ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አንድ ባል ሚስቱ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ወተት እንዲያጠጣት መክረዋል፡፡
 
5፡- ራሷን(ግንባሯን) ይዘህ የሚከተለውን ዱዓ አድርግ👇👇👇
 
ቢስሚላህ አላሁመ ጀንኒብነ ሸየጧነ ወጀንኒብነ ሸይጧኒ ማ ረዘቅተና
 
በአላህ ስም! አላህ ሆይ! ሰይጣንን አርቅልን፤ያበረከትክልንን ነገርም ከሸይጧን አርቅልን)”
 
#እርሷም ግንባርህን ይዛ ይህን ዱዓ ታሰማለች፡፡ ይህ ዱዓ ለወደፊት የትዳር ህይወታህ መቃናት፣ የምትወልዷቸው ልጆች ከሸይጧን እንዲጠበቁና መልካም ልጆች እንዲሆኑ ይረዳል፡፡ትዳሩ ያማረና የሰከነ እንዲሆንም ያግዛል፡፡
 
ይህ የተወዳጁ #ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ሱና ነው፡፡
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group