Translation is not possible.

አባት ሁለት ሴት ልጆቹን ዳረ። አንዷን ለገበሬ አንዷን ደሞ ለሸክላ ሰሪነበር የዳረው፤ ከአመት በኋላ ሊዘይራቸው ብሎ ከአገር ወጣ። ዚያራውን የቤቱ ታላቅ ከሆነችው ለገበሬው ከዳራት ልጁ ጀመረ፤ እሷም እጅግ በደስታ ተቀበለችው።

"እንዴት ነሽ ኑሮ እንዴት ይዞሻል በምንስ እየኖርሽ ነው" ብሎ ጠየቃት

"ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ ነው ያረሰው ፣እህሉን ደግሞ በብድር ነው የወሰደው አሁን ዘርቶታል። ዝናብ እየጠበቅን ነው፤ ከዘነበ ኢንሻአላህ ምርቱ ጥሩ ይሆናል ኑሯችንም ይሻሻላል፤ ካልዘነበ ግን አደጋ ውስጥ ነን።"አለችው

ከዚያም ወደ ሁለተኛ ልጁ አመራ እሷም በደስታ ተቀበለችው።

"ኑሮ እንዴት ነው በምንስ ነው የምትኖሩት"አላት ።

"ባለቤቴ በብድር ነው የሸክላ አፈር የገዛው፤አሁን ብዙ የሸክላ ምርት አዘጋጅቶ መድረቁን እየተጠባበቀ ነው። በየቀኑ ፀሀይ የሚወጣ ከሆነ ምርቱ ይሄድለታል፤በኑሯችን ላይም ለውጥ ይኖራል።የሚዘንብ ከሆነ ግን ሸክላው ይበላሻል።"አለችው

አባት ልጆቹን ከጎበኘ በኋላ ወደ አገሩ ተመለሰ፤ቤቱ ሲደርስ የልጆቹ እናት ስለ ሁኔታቸው ጠየቀችው።እሱም እንዲህ አላት :-

"ከዘነበም አልሃምዱሊላህ በይ ካልዘነበም አልሃምዱሊላህ በይ።"

እንግዲህ የዱንያ ነገር እንዲህ ነው፤ አንዱ የሚፈልገውን ሌላው አይፈልገውም ፤ ላንዱ የሚስማማው ለሌላው አይስማማውም፤ ለአንዱ መሰናክሉ ለሌላው የስኬት መንገዱ ነው። ብናዝንም ብንደሰትም ብናጣም ብናገኝም ቢደላንም ባይደላንም በሁሉም ሁኔታችን ውስጥ አልሃምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀል እንበል።አላህ አመስጋኝ ባሮቹን ይወዳልና

አልሃምዱሊላህ♥♥♥

አልሃምዱሊላህ ♥♥♥

አልሃምዱሊላህ ♥♥♥

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group