Translation is not possible.

ካፈቀራችሁ ዝም ብላችሁ ስለ ፍቅር የተፃፈ ነገር እየተከታተላችሁ ራሳችሁን አትጉዱ! እንደወንድምነት ልምከራችሁ። በምታፈቅሩበት ጊዜ ማድረግ ያለባችሁ ከሁለት አንዱን ነው

1 - ያፈቀራችሁትን ሰው የራሳችሁ ለማድረግ አቅሙ ካላችሁ ቶሎ ወደ ሐላል ግቡ! ካልሆነ ግን የሚያስጠላ የሆነ ህይወት ውስጥ ትገባላችሁ። አደራ ከሐላል ውጭ life በሚል ሙድ ህይወታችሁን እንዳታበላሹ መውጫው የራቀ ነውና

2- የራሳችሁ ማድረግ የምትችሉበት ሁኔታ የራቀ ከሆነ እናንተ ራሳችሁ ራቁ! የወደዳችሁትን ሰው ሊያስታውሳችሁ የሚችለውን ነገር በሙሉ ከህይወታችሁ አስወጡ! ለመርሳት መሞከር የለባችሁም ምክኒያቱም ለመርሳት መሞከር በራሱ ማስታወስ ነው። ስለዚህ ሰበቦቹን በሙሉ ካስወገዳችሁ በኋላ በአሏህ ፍቃድ ከጊዜ ጋር ሁሉም ይረሳል!

ነገር ግን ፍቅር በዚህ ደረጃ ቀላል አይደለም። ልብን የሚሰረስር፣ እንቅልፍን የሚያርቅ፣ ናፍቆትን የሚያወርስ ህመም ነው። ብዙ ሰው በዚህ ህመም ታሟል። ለዚህም ነው ኢብኑል ቀይም " ፍቅር በሽታ ነው መድሐኒቱ ደግሞ ያፈቀሩትን ማግባት ነው" ያለው።

በዚህ ህመም የታመማችሁ አሏህ የምትወዱትን እንድታገቡ አድርጎ ይፈውሳችሁ

𝓱𝓪𝓯𝓾 https://t.me/bintahemed

http://t.me/bintahemed

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group