Translation is not possible.

ሩሲያ የኑክሌር ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የክሩዝ እና ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ያቀፈ የኑክሌር ልምምድ ማድረጓን ክሬምሊን አስታወቀ፡፡

ሙከራው የሞስኮን ወታደራዊ አመራር እና ስልታዊ የኑክሌር ሀይሎች ዝግጁነት ለመገምገም ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

ልምምዱ ሶስት ወታደራዊ ዘርፎችን ያከተተ ነው የተባለ ሲሆን ÷የአህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል ልምምድ፣ኑክሌር የታጠቁ የባህር ሰርጓጅ መርከቦች ልምምድ እና ስትራቴጂካዊ ቦምቦች የልምምዱ አካል ነበሩ ተብሏል፡፡

ልምምዱ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው እና ፕሌስክ ኮስሞድሮም በተባለው የሩሲያ አህጉር አቋራጭ ማስወንጨፊያ ማዕከል መከናወኑን ነው ክሬምሊን የገለፀው፡፡

በእለቱ የተሞከረው ሀገር አቋራች ሚሳኤሉ ከተተኮሰበት ቦታ ከ5 ሺህ 700 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ በሚገኘው የካምችካ ባህረ ገብ መሬት ላይ ኢላማውን መምታቱ ተገልፃል፡፡

ልምምዶቹን በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በሞስኮ የሚገኘው የሩሲያ ብሔራዊ የመከላከያ ኦፕሬሽን ሴንተር አስተባባሪነት የተካሄዱ መሆናቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

FBC

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group