Translation is not possible.

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ውይይት በመቀሌ ከተማ አካሄደ፡፡

ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) የተመራውና ሌሎች አራት ኮሚሽነሮችን ያካተተው ቡድን በመቀሌ ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱ ተመላክቷል፡፡

ቡድኑ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ተገናኝቶ የተወያየ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለመተግበር የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አሰራር ኮሚሽኑ መተግበር እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ኮሚሽኑ እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራት ገላፃ አድርገው ከእነዚህ ባለድርሻ አካላት ሊደረግላቸው የሚገቡ ትብብሮችን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ኮሚሽኑ በክልሉ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ደረጃ በደረጃ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ማከናወን እንደሚገባ በውይይቱ የተመላከተ ሲሆን የክልሉ መንግስት ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጹን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

@Jeilu Tv

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group