Translation is not possible.

ጠራራ ፀሀይ ላይ ከመቃብሮች መሀል ባህሉል የተባለ የከተማው

ዕውቅ እብድ ቁጭ ብሏል። (160 አመተ ሂጅራ)

በግዜው የሙስሊሙን አለም ሲያስተዳድር የነበረው ሀሩነ-ረሺድ

ድንገት ከመቃብር መሀል የተቀመጠውን እብድ ይመለከተዋል።

ንጉስ ሀሩን የማፌዝ ገፅታ እየተነበበበት፦ «አንተ ባህሉል! እንተ

ቆይ መች ነው ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጠራው።

ከመቃብሮች መሀል ብድግ አለ። ዙርያውን በአይኑ ቃኘ'ና

ከአጠገቡ ከምትገኝ ዛፍ ላይ በርጋታ ወጥቶ፦ «አንተ ሀሩን! አንተ

ቀውስ! ቆይ ግን መች ይሁን ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጮኸበት።

ንጉስ ሀሩን የተቀመጠባትን ፈረስ በዝግታ እየጋለበ መጥቶ ከዛፏ

ስር ቆመ።

እዝያው ፈረሱ ጀርባ ላይ ተንደላቅቆ፦ «እንዴ! እኔ ነኝ እብድ ወይስ

በዚ ጠራራ ፀሀይ መቃብሮች ላይ ምትቀመጠው አንተ ነህ

እብድ?»

«እኔማ ጤነኛ ነኝ» አለ ባህሉል፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ

እየተስተዋለበት።

«እንዴት ሆኖ...?» ሀሩን የማሾፍ ስሜት የተቀላቀለበት ጥያቄ

ጠየቀ።

ባህሉልም ወደ ንጉሱ ቤተ-መንግስት እያመላከተ፦ «ያኛው ጠፊ

እንደሆነ አውቃለሁ። ይኸኛው ደግሞ (መቃብር) ዘውታሪ

እንደሆነም አውቃለሁ።

ስለዚህ እኔ ይኸኛውን ከዝያኛው አስበልጬ ገንብቸዋለሁ። አንተ

ደግሞ እንደሚታወቀው ያኛውን ብቻ ገንብተህ ይኸኛውን

አፍርሰኸዋል።

ምንም እንኳን ከገነባኸው ህንፃ ተነቅለህ ወዳፈረስከው መቃብርህ

ወራጅ እንደሆንክ ብታምንም ግን መሄድን አትሻም» ብሎ በአውላላ

የትካዜ ሜዳ ላይ ንጉሱን አደናገረው።

ባህሉል ንግግሩን ቀጥሏል፦ «ታድያ ከኔ እና ከንተ ማናችን ነን

እብድ መባል ያለብን...»

ካማረው ፈረስ ላይ በክብር ቁጭ ያለው ንጉስ ከጉንጮቹ እንደ

ጅረት የሚፈሰው እንባው ፂሙን አረጠበ።

ንጉስ የሀፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ፦ «ባህሉል ሆይ! ወላሂ አንተ

ትክክል ነህ። እባክህ ትንሽ ምክር ጨምርልኝ» አለው።

«ቁርአን ይበቃኻል፤ ምክሮቹን ጠበቅ አድርገህ ያዝ» አለው

ባህሉል።

«እሺ ምትፈልገውን ንገረኝ'ና ልፈፅምልህ» አለው ንጉስ ከግዛቱ

ሊያስጠቅመው።

«አዎን! 3 ምፈልገው ነገር አለ። ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃለሁ»

አለው ባህሉል ከዛፉ ላይ ቁጭ ብሎ።

ንጉስም፦«ጠይቀኝ» አለ፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተነበበ።

ባህሉል፦«እድሜዬን ጨምርልኝ»

ንጉስ፦ «ይኸንን እንኳን አልችልም»

ባህሉል፦ «ከመለከል መውት ጠብቀኝ»

ንጉስ፦ «ኧረ አልችልም»

ባህሉል፦ «እሺ ከእሳት ታድገኸኝ ጀነት አስገባኝ»

ንጉስ፦ «በምን አቅሜ...!»

ባህሉል፦ «አየህ አንተ ባርያ እንጂ ገዢ አይደለህም፤ እኔም ባንተ

የሚፈፀምልኝ ምንም ጉዳይ የለኝም»

-------------------------------------------------------------

ምንጭ፦

ﻛﺘﺎﺏ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group