ተሳፋሪዎች ረስተው የወረዱትን 93ሺ ብር ለባለቤቶቹ የመለሰው አሽከርካሪ
⚡️የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ በነበረበት አጋጣሚ ተሳፋሪዎች ጥለውት የወረዱትን 93 ሺህ ብር ለፖሊስ ማስረከቡን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
⚡️አቶ ይነበብ ቀለሙ የተባለው ግለሰብ በጉዞ ርቀት የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ስራ ላይ የተሰማራ አሽከርካሪ ነው፡፡ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ 93 ማዞሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ ላይ አራት ሰዎችን ጭኖ ጉዞ ይጀምራል፡፡
⚡️ተሳፋሪዎቹን የሚፈልጉት ቦታ አድርሶ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚፈልጉ ግለሰቦችን ለመጫን ሲዘጋጅ የነበረው አቶ ይነበብ ቀለሙ በተሽከርካሪው ውስጥ በጥቁር ፌስታል የተቀለለ 93 ሺህ ተሳፋሪዎቹ ረስተው መውረዳቸውን በመረዳት ገንዘቡን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወስዶ በታማኝነት አስረክቧል፡፡
⚡️የገንዘቡ ባለቤቶች ተሽከርካሪ ውስጥ ብር ረስተው መውረዳቸውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተው ስለነበር ባመለከቱት መሰረት አሽከርካሪው በተገኘበት ገንዘባቸውን ተረክበዋል
⚡️ታማኝነት ከንፁህ ህሊና የሚመነጭ በመሆኑ የሰውን ገንዘብ በሃይል የሚነጥቁ ወንጀለኞች በሚስተዋሉበት በዚህ ወቅት ወድቆ ያገኘውን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከበው ግለሰብ ምስጋና ይገባዋል ያለው ፖሊስ፤ እንዲህ አይነት መልካም ተግባር በሁሉም ሰው ዘንድ ቢለመድ በእርስ በርስ ማህበራዊ ግንኙነት ወቅት የሚፈጠረውን መተማመን ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጿል።