Translation is not possible.

ሴቶችን የመመልከት ልማድ የነበረው የአንድ ወጣት ወደ አንድ

አሊም ዘንድ በመሄድ እንዲህ ሲል ጠየቀ፡

እኔ ራሴን ማላቀቅ ባልቻልኩት መጥፎ ልማድ ውስጥ

ተዘፍቄያለሀ፣ በዚህ ምክንያት የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛል

እኔ በመንገድም ሆነ በገበያ ውስጥ ያሉ ልጃገረዶችን

ከመመልከት እራሴን ማቆም አልቻልኩምና ይህን አጉል ልማድ

ለመተው, ምን ማድረግ አለብኝ ሲል ጠየቀ ?

አሊሙም የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማው ያደረገውን ምክንያት

ሰሙት ....

ከዚያም አሊሙ አንድ ቡርጩቆ አመጡ በቡርጩቆ ውስጥ እስከ

ጫፉ ድረስ የተሞላ ወተት በእጁ አስያዙትና አንድ ሰው እርሱን

እንዲከተለው አድርገው ወደ ገበያ ውስጥ እንዲገባ እና ወጣቱ

ልጅ ከያዘው ቡርጭቆ ውስጥ

አንዲት ጠብታ ወተት እንኳ ቢያፈስ ሰው በተሰበሰበበት ገበያ

መሀል እንዲደበድበው ነገሩት ።

በእርግጥ ወጣቱ አንዲትም ጠብታ ወተት ሳይደፋ መራመድ ችሎ

ወደ አሊሙ ተመለሰ ከዚያም አሊሙ ።

ጠየቁት ፡ በመንገድህ ላይ ስንት ሴት ልጆችን አይተሃል?

ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፡ ትኩረቴ በወተት ብርጭቆ ላይ ብቻ

ስለነበር በዙሪያዬ ማንንም አላየሁም ምክንያቱም ወተቱ ቢፈስስ

በሁሉም ሰው ፊት መመታቴን ፈራሁ አለ

አሊሙም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- የእውነተኛ ሙእሚን ሙስሊም

ጉዳይም ልክ እንደዚሁ ነው።

እውነተኛ ሙእሚን አላህን ይፈራል ሀጢያት ሰርቶ ካለፈ በቂያም

ቀን አላህ ፊት ሲቆም ያፍራል።

እነዚህ አማኞች ሁል ጊዜ የሚያተኩሩት በፍርድ ቀን ላይ ነው

።ስለዚህ ኃጢአትን ከመሥራት ይጠብቃሉ!

አላህ በቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ብሏል፡- ለምእመናን ዓይኖቻቸውን

እንዲያወርዱ (የተከለከሉ ነገሮችን ከመመልከት)፣

ብልቶቻቸውንም እንዲጠብቁ ንገራቸው። ይህ ለእነሱ የበለጠ

ንጹሕ ነው። አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።

አላህ ሀራም ነገሮችን ከመመልከት ይጠብቀን 🤲።

Send as a message
Share on my page
Share in the group