ቢስሚላህ!!
በቀደር(በአሏህ ያለፈ ውሳኔ)በትክክል ያመነ ሰው፣ለሰዎች ይሉኝታ፣መጥቀምም ሆነ መጉዳት፣ቦታ አይሰጥም።
ምክንያቱም እነዝህ ሁሉ በአሏህ እጅ ያሉና ማኑም እንኳን ለሌላ ግለሰብ ለራሱ እንኳን በፈለገው መስመር ሊያስኬዳቸው የማይችል የሆኑ ጉዳዮች ናቸው።
ኣዎ ዋናውና አሳሳቢው"በአንተና በጌታህ መካከል ያለውን ግንኙነት አስተካክል"የሰዎችን ጣጣና ሸር እርሱ አሏህ ይበቃሃል።
ለማኑም ስላጎበደድክ ከወሰነልህ ውጭ ቅንጣት እንኳ የምታገኘው ነገር አይኖርም።ማኑም ስለጠላህ ምንም አትሆንም።ይሄ ባይሆን ኖሮማ የሚጠሉህ ሺሆች ኢያሉ በዝህ ሁሉ የጌታህ ፀጋ ባልተንበሻበሽክ ነበር።
እርግጥ ነው ጠላት ለነቢዩም ሰ ዐ ወ አልጠፋም፣ነገር ግን መልካሞች ሁሉ ይወዷቸዋል(በሚዛን የሚሰፍረው ውዴታም የመልካሞቹ ብቻ ስለሆነ)።
ሰይጣንና ጭፍራው ወዳጆቻቸውን እንጂ የአሏህን ወዳጆች ስለማይወዱ ከሷሊሆች ለመሆን ከጣርክ የጧሊሆቹን ተንኮል ከጉያቸው ያስቀርልሃል።
እድሜህ፣ሪዝቅህ፣ሌሎችም እጣፈንታዎችህ በአሏህ መዝገብ ላይ ተወስነው ያለቀላቸው በመሆኑ፣ለዓለማዊ ጥቅም ብለህ፣በዲንህ፣በሱናህ፣በኢስላማዊው ዒዝዛህ(ክብርህ)ላይ አትቆምር።
ይሄኔ የሚከተሉትን በቀደር የማመንን ጥቅሞች(ሰመረህ)ትጎናፀፋለህ፦
― ተውሂድን ማረጋገጥን፣
― ከአሏህ ሂዳያን(መመራትን)እና የኢማን ጭማሬን፣
― ኢኽላስን(ለአሏህ ብቻ ብሎ መስራትን)፣
― በአሏህ ብቻ መመካትን(ተወኩልን)፣
― አሏህን ብቻ መፍራትን፣
― በሚደርስብህ ችግር ላይ ትዕግስትን፣
― አሏህ የወሰነልህን መውደድን፣
― በተሰጠህ መብቃቃት፣ለሌሎች በስልጣናቸውና በገንዘባቸው ሰበብ የማታጎበድድ፣እንዲሁም ከምቀኝነት የፀዳህ ሙስሊም መሆንን አሏህ ያጎናፅፈሃል።